in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c
ይህቺ ልጅ ትናንት ራሷን አጠፋች ተብሎ ወሬው እዚህ ሰፈር እየተዘዋወረ ነው። እኔ ልጅቷን አላውቃትም። በስሟ ሰርች አድርጌ ገብቼ እዚህ ፖስት ላይ ትላንት ልጅቷ በህይወት እያለች የተሰጠውን ኮሜንት ሳይ ከሁለት ወይም ከሶስት አይበልጥም።
ዛሬ ራሷን አጠፋች ከተባለ በኋላ የተሰጠውን ከ 100 በላይ ኮሜንት ሳይ ግን ሁሉም ጓደኞቿ "እባክሽ አዋሪኝ... ፈጣሪዬ ውሸት ነው በለኝ... ምናለበት ባዋራሁሽ ኖሮ... bla bla" እያሉ በአስመሳይ ቃላት እሷ በሌለችበት ኮሜንት ላይ የውሸት እንባ ያነባሉ።
ልክ እንደዚህ ሁሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እዚህ ሰፈር አንዳንድ ወጣቶች ራሳቸውን አጠፉ እየተባለ ፎቷቸው ሲለቀቅ አያለሁ። ራሳቸውን ለምን ያጠፋሉ የሚለው ራሱን የቻለ ምርመራና ጥናት የሚጠይቅ ነገር ቢሆንም እከሌ ራሱን ከማጥፋቱ በፊት እንደዚህ ብሎ ፅፎ ነበር... እከሌ ራሷን ከማጥፋቷ በፊት እንደዚህ ብላ ፅፋ ነበር እያላችሁ ስክሪንሻት አድርጋችሁ ፖስት የምታደርጉ ሰዎች ግን በጣም አስገራሚዎች ናችሁ።
ማንም ሰው ማንንም የመርዳት እና ምክር የመስጠት ግዴታ ባይኖርበትም ሰው ራሱን ካጠፋ በኋላ እዚህ መጥተህ "ብንደርሰለት ኖሮ... ውሸትህን ነው በለኝ... ስንት ነገር አውርተን... እኔ እኮ ቀልድህን ነበር የመሰለኝ... ሳይኮሎጂካል ችግር ሊሆን ይችላል ብናዋራው ኖሮ..." ምናምን እያልክ በአስመሳይ ሀዘን በሰው ሞት ስትደበር ግን በጣም ነው የምፀየፍህ።
ከቻልክ ሰውን በህይወት እያለ አግዘው። ምንም ሳታደርግ ቁጭ ብለህ አይተኸው ከሞተ በኋላ አዚህ ለላይክ መሸቀያ የሀዘን ቅርፅ መስራት ግን በጣም ይደብራል። አንተ ለምን አታግዝም ካልከኝ እኔ እንዳንተ አስመሳይ አይደለሁም። በእርግጥ በእንደዚህ አይነት ችግር ውስጥ ያለን ሰው አግዤ አላውቅም... ግን ቢያንስ የውሸት ለቅሶ አላለቅስም።
1 - 0
Messi tube SUBSCRIBE bemadreg beteseb yihunu💞
yeteleyayu dinawī yehonu hādisochi k’ure’āni tagenyubetalachihu 😍😍