Channel Avatar

Tefer media21 / #ጠፈር ሚድያሚድያ21 @UCuKiYwhRZmYVoQ8AhmCPXag@youtube.com

746 subscribers - no pronouns :c

ወቅታዊ የቤተክርስቲያን መረጃዎች እና ትምህርቶች ሌላ በቤተክርስቲያናችን በኩል እና በእምነ


Welcoem to posts!!

in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c

Tefer media21 / #ጠፈር ሚድያሚድያ21
Posted 1 week ago

🛑   እድሜ ጊዜ ነው ።

ሰው ሞተ የሚባለው ጊዜው ሲያልቅ ነውኮ!

ጊዜ ሲረዝም እድሜ ኖረው
ሲያጥር ሞተ ይባላል ።

ታዳ ሞት ምንድንነው ????

ሞት መራራ ነው ።

ሞት መራራ ከሆነ!!!

ጊዜ ማባከን ምንድንነው ?????

ታዳ ሞት መራራ ከሆነ ጊዜ መባከን
ቢያንስ ህመም ለምን ህመም አይሆንብንም  ??????😓😓😓😓

ሰው ቀጥረህ ስትቀር ከዕድሜህ
(ሰው ቀጥሮህ ሲቀር) ከእድሜህ እየቀነሰ ነው ::

ሰው ገንዘብህን ቢወስድብህ የሆነ ቀን ሊመልስልህ ይችላል ።

ጊዜህን የወሰደብህ ሰው ግን መቸም ሊመልስልህ አይችልም ።



አንድ ሊቅ እንዲህ አለ

በዚህ ዓለም ትልቁ ስጦታ ጊዜ ነው አሉ

ለምን ሲሏቸው  ????

ሰው ጊዜ ሲሰጥህ ከዕድሜው እየቀነሰ ነው አሉ!!!!!


ለዚህ ነው ሴቶችም (ወንዶችም) በፍቅር ውስጥ ሲሆኑ   የማፍቀራቸው ማስረጃ ጊዜ መስጠት ይሆናል !!!




እኛም ቢያንስ ጊዜ ለሰጠን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ቢያንስ የጸሎት ጊዜ አለመስጠታችን  ምን ያህል ሰነፎች እና ዝንጉዎች

ወይም ለእግዚአብሔር ፍቅር የሌለን ነን ምክንያቱም
አንድ ወንድ ወይም ሴት ለፍረኛቸው የሚሰጡትን እና የሚያስቡለትን ያህል ስናስብ በመቅረታችን 😭😭😭😭


ቢያንስ ግማሽ   😭😭😭😭


ቢያንስ እሩብ የለም 😭😭😭😭😭

ሰው ስለፍቅረኛው 24 ሰዓት  አስባለሁ ይላል ።
ያም ባይሆን 12  ሰዓት


ታዳ እግዚአብሔርን  በቀን ለ1 ሰዓት ለምን ማሰብ አቃተን ?????😭😭😭😭😭



ኧረ ለደቂቃዎች ????


አልቻልንም :::

ጊዜን ለሰጠን አምላክ በጊዜ ብናስበው ይበዛበት ይሆን ???????


ካላነሰበትስ ከተጸነስንበት ጊዜ ጀምረን እስከ ዘለዓለም ድረስ ሚሊዮን ጊዜ ተሰጥቶን ብናስበውም
አይበቃንም!!!!!


ስለዚህ በጸሎት
በፍጥረታት ሁሉ
በጊዜያት ሁሉ
እንድናስበው የድንግል ማርያም ልጅ ህያወ ባህርይ ኢየሱስ ክርስቶስ ይርዳን ።


አሜን ::


በጸሎት አስቡኝ።

መጋ  ብሉ ወሐ  መ     ግ


ጠፈር  ሚድያ 21

የቴሌ ግራም ግሩፕ

@sew_bihon


ድንግል ማርያም ሆይ እኔን ለእኔ አትተይኝ አሜን 😭🙏🙏🙏🙏🙏
Me G
በጸሎት አስቡኝ።

4 - 0

Tefer media21 / #ጠፈር ሚድያሚድያ21
Posted 1 month ago

ክፍል 1 ክፍል 2 3 4
ይጠብቁን

3 - 2

Tefer media21 / #ጠፈር ሚድያሚድያ21
Posted 4 months ago

ዝንቱ መስቀል መንበረ ነበልባል
ዘኪሩቤል ቢጽ
አምሳለ ስምኪ ማርያም ርቡአ ኆኅያት ወገጽ
.....
እንቋ አብጽሐክሙ ለብርሃነ መስቀሉ


ድንግል ሆይ እኔን ለእኔ አትተይኝ 🙏

Me G

6 - 1

Tefer media21 / #ጠፈር ሚድያሚድያ21
Posted 6 months ago

ትርጓሜ

18 - 0

Tefer media21 / #ጠፈር ሚድያሚድያ21
Posted 6 months ago

🛑 ሰው እንደ መከር ነው

እኩሉ ሲዘራ እኩሉ ስታጨድ እኩሉ ሲበቅል .......

ጌታ ሆይ በግማሽ አመቴ አትውሰደኝ😭😭😭😭



የሞቱትን ነፍስ ይማር 💔💔😭😭😭


ያሉትን ያጽናናልን አሜን 😭😭😭😭😭😭🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ጠፈር ሚድያ21
Tefer media21

15 - 2

Tefer media21 / #ጠፈር ሚድያሚድያ21
Posted 7 months ago

ክፍል 1 እና 2 ይጠብቁን

ሰላመ እግዚአብሔር የኀሉ ምስሌነ...

21 - 2

Tefer media21 / #ጠፈር ሚድያሚድያ21
Posted 8 months ago

ክፍል 3 ይጠብቁን

13 - 0

Tefer media21 / #ጠፈር ሚድያሚድያ21
Posted 8 months ago

🛑 ክፍል 1 ይጠብቁን

16 - 4

Tefer media21 / #ጠፈር ሚድያሚድያ21
Posted 8 months ago

🛑ክፍል ፩

፩ኛ ወላዲ መለኮት ተወላዲ መለኮት ሠራጺ መለኮት ማለት እንዳይገባ ይናገራል ጥያቄ፡- ወላዲ መለኮት ተወላዲ መለኮት ሠራጺ መለኮት ማለት አይገባምን? መልስ፦ ምንም ቢሆን ወላዲው፣ ተወላዲ ሠራጺ፣ ተወላዲውም፣ ወላዲ ሠራጺ፣ ሠራጺውም፣ ወላዲ ተወላዲ ሊሆን የማይችል ነው:: አካላትን ቅሉ፣ ልዩ ልዩ የሚያሰኛቸው ይህ ወላዲ፣ ተወለዲ፣ ሠራጺ የሚለው ንባብ ነው:: መለኮትን አካላት በሚለያዩበት ስም ጠርቶ ወላዲ መለኮት፣ ተወላዲ መለኮት፣ ሠራጺ መለኮት ማለት መለኮትን እንደ አካላት ሦስት ማለት እንደሆነ አስተዋይ ልቦና ይረዳዋል::
እንዲህም ከሆነ ሊቃውንት በየአንቀጹ “ይሤለሱ በአካላት፣ ወይትወሐዱ በመለኮት'' ያሉት ንባብ ሐሰት ሆነ ማለት ነዋ::
መለኮት በራሱ ወላዲ፣ ተወላዲ፣ ሠራጺ ከተባለ፣ ሦስት በመሆኑ የመንገዱ ጥርጊያ ወደ ዮሐንስ ተዐቃቢ ቤት የሚያገባ መሆኑ አይጠረጠርም::

መለኮትን ወላዲ፣ ተወለዲ፣ ሠራጺ ማለትም፣ ሦስቱ አካላት መለኮት፣ መለኮት፣ መለኮት፣ የተባሉበትን ምሥጢር ባለማስተዋል የታሰበ ስሕተት ነው::
ሊቃውንት ሦስቱን አካላት መለኮት፣ መለኮት፣ መለኮት፣ ብለው ማመናቸው መለኮት በአካል ልዩ ነው ብለው አይደለም::
አንድ መለኮት በሦስት አካላት ልዩ ነው ብለው አይደለም:: አንድ መለኮት በሦስት አካላት ህልው ነው ብለው ነው እንጂ::
፡- ፳፯ኛ ሊቅ ጎርጎርዮስ ነባቤ መለኮት:- ንባብ፡- “ወኢይትሀበሉ ሕጉላን ያብኡ ውስተ ቅድስት ሥላሴ ፍልጠተ መለኮት፣ ወኢድማሬ አካላት፣ ወኢንሰግድ ለ፫ቱ አማልክት፣ አላ ለ፩ አምላክ::
ወንሰምዮሙ በ፫ አስማት፣ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ፣ ፩ መለኮት፣ ወ ፩ ኃይል፣ እንዘ ፫ አካላት እኁዛን በጽምረተ ፩ መለኮት ወህላዌ” ትርጓሜ፦ "ከዕውቀት የተሳሳቱ ሰዎች ልዩ በሆነች ሦስትነት፣ የመለኮትን ልዩነት፣ የአካላትን አንድነት አግብተው ይናገሩ ዘንድ አይድፈሩ፣ ለአንድ አምላክ እንሰግዳለን እንጂ ፣ለሦስት አማልክት አንሰግድምና፣ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ፣ብለን በሦስት ስሞች እንጠራቸዋለን::
እኒህም ሦስቱ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ፣ ባንድ መለኮትና/ሕይወት/ በአንድ ሕልውና አንድነት የተገናዘቡ ሦስት ሲሆኑ፣ አንድ ባሕርይ፣ አንድ ኃይል ናቸው" ብሏልና:: (ድርሳን ፩ ሃይማኖተ አበው) ባስልዮስ ዘአንጾኪያም ፵፩ኛ:-
ንባብ፡- “እንሰ ሶበ እቤ እግዚአብሔር፣ ዕብል በእንተ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፣ እስመ አሐዱ ውእቱ መለኮተ ሥላሴ፣ ወሠለስቲሆሙ አሐዱ እሙንቱ በመለኮት፣ ወእሙነ እብል ከመ እሙንቱ መለኮት ወህላዌ፣ ወለለ አሐዱ እምአካላተ ሠላሴ፣ ያበጽሕ

(ከታተመው ሃይማኖተ አበው ጎርጎርዮስ ነባቤ መለኮት ምዕ ፷፥፮-፯ ይመልከቱ)


ፍጹመ መለኮት፣ ምስለ ዚአሁ አካል ወስም'' (ክፍል ፩ ሃይማኖተ አበው)

ትርጓሜ፡- "እኔ እግዚአብሔር ባልሁ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ማለትን ስለ አብ፣ ስለ ወልድ፣ ስለ መንፈስ ቅዱስ እናገራለሁ:: የሦስቱ መለኮት አንድ ነውና::
ሦስቱም በመለኮት አንድ ናቸው::

እኒህም መለኮትና/ሕይወት/ ሕልውና/ባሕርይ/ እንዲባሉ በእውነት እናገራለሁ::

ልዩ ሦስትነት ካላቸው አካላትም፣ አንዱም አንዱም ከገንዘቡ አካልና ከገንዘቡ ስም ጋራ ፍጹም መለኮትን ገንዘብ ያደርጋሉ" ብሏል::
፯ኛው ሊቅ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያም:- ንባብ፦ “እሉ ሠለስቱ አካላት ፍጹማን ዲበ መንበረ ስብሐት፣ ወእኁዛን በፅምረተ አሐዱ መለኮት፣ ዘውእቱ አሐዱ ብርሃን ዘይሠርቅ እምኔሁ ሥላሴ”

ትርጓሜ፡- “እኒህ ሦስቱ አካላት በጌትነት ዙፋን ላይ ያሉ ፍጹማን ናቸው:: በአንዱ መለኮት አንድ አድራጊነትም የተገናዘቡ ናቸው::
ይህም መለኮት/ባሕርይ/ የአካል ሦስትነት ከሱ የሚገኝለት አንድ ብርሃን ነው” ብሏል::
(ክፍል ፩ ሃይማኖተ አበው) አቡሊዲስ ዘሮምም.፲፫ ሊቅ:- 20

ንባብ፦ “ወልድኒ ቃሎሙ ለአብ ወለመንፈስ ቅዱስ፣ ወመንፈስ ቅዱስኒ መንፈሶሙ ለአብ ወወልድ፣ ወበዝንቱ አእምርነ ከመ ፩መለኮተ ሥላሴ፣ ወሎቱ ንሰግድ፣ ወአበዊነሂ እለተጋብኡ በኒቅያ

(19 ዝኒ ከማሁ ሃይማኖተ አበው ምዕ ፷፮፥፮-፯ ከታተመው ሃይማኖተ አበው ምዕ ፲፩፥፰-፱ ይመልከቱ )


ይቤሉ እመቦ ዘይፈልጥ መለኮቶ ለእግዚአብሔር አብ እምወልድ ወእም መንፈስ ቅዱስ ውጉዘ ለይኩን::'

' ትርጓሜ፦ “ወልድ ለአብና ለመንፈስ ቅዱስ ቃላቸው ነው::
መንፈስ ቅዱስ ለአብና ለወልድ እስትንፋሳቸው ነው::
በዚህም የምንሰግድለት የሦስቱ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ መለኮት አንድ እንደሆነ አወቅን::
በኒቅያ የተሰበሰቡ አባቶቻችንም የአብን መለኮት ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ የሚለይ ሰው ቢኖር የተለየ ይሁን ብለዋል'' ብሏል::
(ክፍል ፩ ሃይማኖተ አበው) 21 ይህን የመሰለ በየአንቀጹ የተነገረ ብዙ ነው::

ሐተታ ሦስቱ መለኮት፣ መለኮት፣ መለኮት መባላቸው አንድ መለኮት በሦስቱ አካላት ሕልው ሆኖ፣ ሦስቱን አካላት ስለአገናዘበ ነው እንጂ መለኮት በአካል የተለየ ሆኖ እንዳይደለ አስተዋይ ልቦና ያለው ሰው መጻሕፍትን በጥንቃቄ ቢመረምር ይረዳዋል::
መለኮት በአካል የተለየ ቢሆን፣ ሦስቱ ሁሉ ባልተጠሩበትም ነበር::
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ መባል ግን፣ በአካል የተለየ ቢሆን በየራሳቸው ተጠሩበት እንጂ ሦስቱ ሁሉ እንዳልተጠሩበት።

( 21 ዝኒ ከማሁ ሃይማኖተ አበው ምዕ ፴፱፥፰-፱ )



አስተወለን እናንብብ

የቴሌ ግራም ግሩፕ

@sew_bihon


ድንግል ማርያም ሆይ እኔን ለእኔ አትተይኝ አሜን 😭🙏🙏🙏🙏🙏
Me G
በጸሎት አስቡኝ።

16 - 1

Tefer media21 / #ጠፈር ሚድያሚድያ21
Posted 8 months ago

🛑ተሰአሎ ለአቡከ ወይነግረከ ወለሊቃውንቲከ ይዜንውከ

6 - 0