Channel Avatar

Nejashi TV @UCriMjuMrhDlxSzieh5NnLYQ@youtube.com

462K subscribers - no pronouns :c

Nejashi TV, a united platform born from the coalition of thr


Welcoem to posts!!

in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c

Nejashi TV
Posted 1 year ago

.

2 - 0

Nejashi TV
Posted 1 year ago

.

7 - 0

Nejashi TV
Posted 1 year ago

.

4 - 0

Nejashi TV
Posted 1 year ago

.

3 - 1

Nejashi TV
Posted 1 year ago

T

9 - 1

Nejashi TV
Posted 1 year ago

Ramzin

10 - 1

Nejashi TV
Posted 3 years ago

ሀገሬ ቲዩብን በመቀላልቀል ጥሩ ጥሩ ቪዲዮዎችን ይኮምኩሙ
www.youtube.com/channel/UCVhy...

127 - 8

Nejashi TV
Posted 4 years ago

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ህልፈትን ተከትሎ በሻሸመኔ ከተማ የደረሱ ጥፋቶችን ሙስሊሞች የፈፀሙት እንደሆነ ተደርጎ መዘገቡ አግባብነት የሌለው እና መሰረተ ቢስ መሆኑን ቢላል ሚዲያ ማጣራት ችሏል ።
******

የሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ማግስት ለኢትዮጵያ ከባድ ጊዜ ነበር። ከመዲናዋ አዲስ አበባ እስከ ባሌ፣ ከዶዶላ እስከ ኔጌሌ በተለያዩ ከተሞች ከባድ ተቃውሞ ነበር። አንዳንድ ቦታዎች ላይ ተቃውሞው ወዲያው ሲበርድ ሌሎች ቦታዎች ላይ ደግሞ ወደ ጥቃት አምርቶ በታሪካችን ላይ ጥቁር ጠባሳን ጥሎ አልፏል።

ምዕራብ አርሲ ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጪ ከነበሩባቸው ቦታዎች ውስጥ አንዱ ነበር። በተለይም ሻሸመኔና ዝዋይ/ባቱ የበርካታ ሰዎች ውድ ህይወት ያለፈትና ለፍተው ጥረው ግረው ያፈሩት የላባቸው ጥሪት የወደመበት እና ከሁሉ በላይ አብሮ የመኖር እሴታቸው የተናደበት ወቅት ነበር። ጥፋቱ ሃይማኖት እና ዘርን የለየ ሳይሆን ሁሉንም በአንድ ጨፍልቆ ሃገር የማውደም ተልእኮ የነበረው መሆኑን የመንግስት ሚዲያዎችም ጭምር እየዘገቡት ነው ።

ይሁንና ይህንን ሁነት ተከትሎም አላማቸው ግልፅ ባልሆነ አካላት እና ሚዲያዎች ከፍተኛ የሆነ ሙስሊሙን የማንቋሸሽ ዘመቻ ተከፍቶብናል። ጥቃቱን ሙስሊም ጠል ሀይሎች ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ለማሸማቀቅ ሲሞክሩበት በተደጋጋሚ ታይቷል። በግጭቱ የተጎዱ ሙስሊሞችን ከመደበቅ ጀምሮ ንብረታቸው የወደመባቸውን ሙስሊሞች ከሚዲያ የመሰወር ከፍተኛ ደባ ተፈፅሟል። ሀሰተኛ መረጃዎችን እና ትርክቶችን ተጠቅመው ሀገሪቷ በሀይማኖት ግጭት እንድትታመስ የሚሰሩ ሀይሎችንም ማየት ችለናል።

ለምሳሌ የኔታ የተባለ ሚዲያ ሻሸመኔ ላይ የዘጠኝ ወር ነፍሰ-ጡር በልጆቿ ፊት ታርዳ ተገደለች በማለት የሀሰት መረጃን ለጥፎ ብዙዎች ተቀባብለውታል።

ሆን ብለው ሙስሊሙን ለማጠልሸት ያቀናበሩት ዘገባ መሆኑን ሁሉም ሊረዳው ይገባል። እኛም ሻሸመኔ ደውለን አነጋግረን ነበር።

በሀጫሉ ሞት ማግስት ሻሸመኔ ላይ በተፈጠረው ረብሻ የደረሰውን ነገር ሁሉም ሰው የሚያውቀው ነው። እኛም ባጣራነው መሰረት በቡድን ያሉ ሰዎች
የሟችን ቤተሰብ በር አንኳኩተው በሀይልም ለመግባት ሲሞክሩ ሟች ሜሮን ተስፋዬ በሩን ከፍታ ከቤተሰቧ ጋር ግብግብ ይጀመራል ። እንደነገሩን ሰዎች መረጃ በዚህ መሃል ነው እንግዲህ ነብሰ ጡሯ ሜሮን ተገፈታትራ የወደቀችው። ወዲያው ወደ ሃዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ተወስዳ ህክምና ቢደረግላትም በጣም አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ከቀናት ህክምና በኋላ ህይወቷ አለፈ።

"አማራ አይወለድም ። ክርስቲያን አይወለድም" እያሉ እንደ አረዷት ተደርጎ ያቀረቡት ውሸት ብቻ ሳይሆን ህዝብን ከህዝብ ከፋፍሎ በዘርና ሀይማኖት የሚያጋጭ እጅግ አደገኛ መርዝ ነው።

በዩቲዩብ ቻናሎች የሆኑት የኛ ቲዩብና የኔታ ቲዩብ በለቀቁት ቪዲዮ ላይ ባለቤቷ "አረዷት" የሚል ቃል ባይጠቀምም ሚዲያዎቹ ሆን ብለው በፅሁፍ ይህን ቃል ተጠቅመው የተዛባ መረጃን ሲያስተላልፉ ሌላው ህዝብ ደግሞ «የ9 ወር ባለቤቱን ልጆቿ ፊት አረዷት» እያለ ይህንን የተሳሳተ ዘገባ አሰራጭቷል።

ሻሸመኔ ስለተከሰተው ዝርዝር መረጃ ቢላል ሚድያ ጉዳዩን ተከታትሎ ሰፋ ባለ መልኩ እውነታውን በሚያሳይ መልኩ ያቀርባል ። በተለይም ድምፃቸው እንዳይሰማ የተደረጉት የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ሙስሊሞች ጉዳይ ላይ ትኩረት እንሰጣለን።

የህዝቦች አንድነትና የሀገር ሰላም ጉዳይ አንዱ ትልቁ አጀንዳችን ነውና በተከታታይ የተዛቡ መረጃዎችን ማረማችንን እንቀጥላለን። ለሟች ባለቤት፣ ልጆችና በዚህ ከባድ ጊዜ ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን። መንግስትም ይህንን የሃሰት ትርክት በመፍጠር በህዝቦች መሃከል መቃቃርን ለመፍጠር የሚሰሩ አካላትን ተገቢውን እርምት እንዲያደርጉ እርምጆ መውሰድ አለበት የሚል መልእክት አለን ።

491 - 73

Nejashi TV
Posted 4 years ago

2.4K - 142