Channel Avatar

አዩቲ wollo media 1⃣ @UCo7p588PqwSb1XmOMb2lEZQ@youtube.com

6.3K subscribers - no pronouns :c

አሰላም አሊይኩም ወራህመቱላሂ ወበርካቱሁ አዩቲ wollo media 1⃣ በዚህ ቻናልም አዝናኝና


Welcoem to posts!!

in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c

አዩቲ wollo media 1⃣
Posted 1 day ago

@ ما شاء الله

0 - 0

አዩቲ wollo media 1⃣
Posted 2 days ago

ማሻ አላህ

0 - 0

አዩቲ wollo media 1⃣
Posted 5 days ago

አትጨነቁ
〰〰〰

ክፍል 3⃣7⃣
〰〰〰〰

5⃣ በቀዷና ቀደር ማመን
〰〰〰〰〰〰〰〰

«በፍጥረተ አለሙ ውስጥ እየሆነ ያለው ሁሉ በአላህ ፈቃድና ይሁንታ ነው። ከእሱ እውቅናና ፈቃድ ውጭ አንድም የሚሆን ነገር የለም። ከእምነት ማዕዘናት አንዱ የሆነውን ቀደርን ከልብ መቀበል ውስጥን ያረጋጋል። በባለፉ ውሳኔዎቻችን እንዳንቆጭና በወደፊቶችም ላይ የበለጠ ተስፋ እንድንጥል ያደርገናል። ቀደር ለምዕመናን የውስጥ እረፍትን ይለግሳል።

« ሁሉም ነገር አላህ ከወሰነው ልክ እንደማያልፍ ያሳያል። ያገኘን ነገር እንደሚያገኘን ቀድሞውኑ ተፅፏል። ያላገኘን ደግሞ እንደማያገኘን ቀድሞውኑ ተከትቧል። በዚህም መውደድ ግድ ነው። ስለዚህ ይህ ኢስላማዊ አስተሳሰብ ፈተናዎችን አቅልለን እንዲናይ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ቀላል አይደለምና ቀደርን ከልብ እንቀበል።

6⃣ ሰብር ማድረግ
〰〰〰〰〰〰

«ተግባሩ ላይ ነው እንጅ የደከመን የሰብርን ጥቅም ሁላችንም እንረዳለን ። ዋጋውንም ምን ያህል እንደሆነ እናውቃለን ። አላህ (ሱ•ወ) እንዲህ ይላል፦

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ إِنَّ اللَّهَ مَعَ الصَّابِرِينَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በመታገስና በሶላት ተረዱ፡፡ አላህ (በእርዳታው) ከታጋሾች ጋር ነውና፡፡

«ከሰብር ጋር ሁሌም ድል አለ። ከሰብር ጋር ስኬት አለ። በተለይ የተነሳንለት አላማ ኖሮን ለጊዜው ያልተሳካልን እንደሆነ ሰብር በማድረግ ጊዜን መጠበቁ ሌላ አላማ ነው። የባሰ ጥፋት ይመጣል ተብሎ የተፈራ እንደሆነም ከሰብር ውጭ አማራጭ ሊኖር አይገባም።

7⃣ ወንጀልን መራቅ
〰〰〰〰〰〰〰

«ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የታዘዝንበትን ነገር በተቻለን መጠን እንዲንሰራ ያዘዙን ሲሆን ወንጀልን ግን ከናካቴው እንድንርቅ ነው የመከሩን። በቀውጢ ጊዜ ከወንጀል መራቅ በተለይ ራስንም ሆነ ሌሎችን ከመበደ መራቅ ያለው አስተዋፅኦ ቀላል አይደለም።

‹ሰውን መበደልና የሌላውን መብት መጋፋት የአንድን ሰው ልመና ምላሽ ከሚነፍጉ ነገር መካከል በዋናነት ይጠቀሳሉ። ስለሆነም በሁሉም መልኩ ወንጀል የተባለውን መራቅ ግድ ይለናል።

8⃣ እውቀት
〰〰〰〰

እውቀትን ዲናችን ከፍ ያደረጋት ቢሆንም እኛ ዋጋዋን አሳንሰናል። ቁርአንና ሀድስ ቢያወድሷትም እኛ ንቀናታል። ዲናዊም ሆነ አለማዊ እውቀት ማህበረሰቡን ለማንቃት ፣ ስነ-ምግባሩን ለማምጠቅና ፣ልማትን ለማፋጠን ያላቸው ሚና ቀላል አይደለም። እውቀትና መረጃ የሰው ልጅ ሌላው ቀርቶ አምላኩን እንዴት መገዛት እንዳለበት ሊያውቅ አይችልም።

«በመሆኑም ሁላችንም ለእውቀትና ለትምህርት ያለን አመለካከት መቀየር ይኖርብናል። ከጊዜው ጋር ለመሄድና በመረጃ ቀድሞ ለመገኘት ማወቅና መማር የግድ ይለናል። ባወቅን ቁጥር ነገሮችን እንዴት ማስኬድ እንዳለብን ፣ ፈተናዎችን እንዴት እንደምንወጣ እናውቃለን።

«የአላህ መልዕክተኛ (ሰሰላሁ አለይሂ ወሰለም ) ስለ እውቀት ደርጃ ሲናገሩ ፣ እውቀትን ፍለጋ መንገድ የጀመረ ሰው አላህ በዚያው ምክንያት ወደ ጀነት መንገድን ያገራለታል። መላኢኮች እውቀት ፈላጊ የሚሰራውን ነገር በመውደድ ክንፋቸውን ይዘረጉለታል። ዓሊም ለሆነ ሰው በሰማይና በምድር ውስጥ ያለ ሁሉ ፣ የባህር አሳዎችም ሳይቀሩ ከአላህ ምህረት ይጠይቁለታል።

«እውቀት ያለው ሰው አላህን በሚያመልከው ያለው ደግሞ ጨረቃ በሌሎች ከዋክብት ላይ ደምቃ እንደምትታየው ነው። ዑለሞች የነብያት ወራሾች ናቸው። ነብያቶች ደግሞ ውቀትን እንጅ ዲባርም ሆነ ዲረሃምን (ወርቅና ብርን )አላወረሱም ። ዕውቀትን የያዘ ትልቅ ነገር ያዘ ። ብለዋል። ስለሆነም እውቀትን እንፈልግ ። ለማወቅ ሁሌ እንጣር።

9⃣ መልካም ስነ-ምግባር
〰〰〰〰〰〰〰〰

«አንድ በአላህ ያመነ ሰው ስራውን በአላህ ማመን ብቻ ላይ መገደብ የለበትም። የእምነቱ ነፀብራቅ መልካም ስነ-ምግባር ፣ መልካም ባህሪያቶችም መስፋት ይኖርበታል። አካሄዱም የተለያዩ እምነት ተከታዮችን በማይጌዳ መልኩ መሆን ይኖርበታል። ካልሆነ ለውጫዊ ገፅታው እንጅ ለቁምነገሩ የማይጨነቅ ባዶ እምነትና አስመሳይ ሃይማኖተኝነት ሊከተል ይችላል። የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከእናንተ ውስጥ የትንሳኤ ቀን ወደ እኔ ቀርቦ የሚቀመጠው በስነ-ምግባሩ ምርጣችሁ የሆነ ሰው ነው። ብለዋል።

«በመሆኑም ስኬቶቻችን ይበዙ ዘንድ የስነ-ምግባራችን ዋጋ ከፍ ማለት አለበት። ዛሬ ላይ በተለይ ውጫዊ የሆኑ ፈተናዎችንና መሰናክሎችን ማለፍ የምንችለው በሰከነና ብስለት በተሞላበት መልካም ስነ-ምግባር ነው። ምርጥ ስነ-ምግባሩንና ባህሪዎቹን የጠበቀ ሰው ከራሱ አልፎ ማህበረሰብንም መለወጥ ይችላል።

መጨረሻችን ምን ይሆን.....!
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

የሰው ልጅ ምድር ላይ ሲኖር አጀማመሩ ሳይሆን ፍፃሜው ነው ሚታየው። መርጀመር ሁሉም ይጀምሬል ፍፃሜው ነው ለብዙዎች የማይሳካው። መልካምን ነገር በጀመሩት ልክ መግፋት ከባድ ነው። ጀምሮ የሚቋርጥ፣ መሃል ደርሶ ሚያቆም፣ ጫፍ ደርሶ የሚደክም ብዙ ነው። አላህ (ሱ•ወ) የመጀመሪያውን የሕይወታችን ምዕራፍ እንደፃፈ ሁሉ የመጨረሻዋንም ገፅ ፅፏል።

«ጅምሬንም ሆነ ፍፃሜየን የሚያሳምረው እሱ ነው። አላህ ( ሱ•ወ ) ነገሮችን መቋጨት ፈለገ ግድ የለውም። አይደለም የተራ ሰዎች አምባገነኖችንና ትዕቢተኞች ሁሉ ለእሱ አይከብዱትም።

የአምባገነኖች መጨረሻ ምን ይሆን!
<~~~~~~~~~~~~~~~~~~>

«ስልጣን ሁሉ የአላህ (ሱ•ወ) ብቻ ነው። ፍፁም ፍትሃዊ የሆነውም እሱ ብቻ ነው። በምድር ላይ ከእኔ በላይ ማንም የለም ። በማለት የሰው ልጅን የበደሉ ፣ያሰሩ ፣ ለስደት የዳረጉና የገደሉ ሁሉ........መጨረሻቸቅ የከፋ ነው የሚሆነው። ሁሉን አዋቂና ተቆጣጣሪ የሆነው ጌታ ቢያቆይላቸው እንጅ አይረሳላቸውም።

~> የነምሩድ ጉዳይ እዚህ ግባ በማትባል በትንሽ ትንኝ ተፈፀመ።
~>የፊርዐውን ጉዳይ በባህር ውስጥ በመስጠም ተቋጨ።
~> የአብረሃ ነገር በተጠበሱ የጀሃነም ድንጋዮች ፍፃሜ አገኘ።
~> የኡመያህ ጉዳይ ቢላል በሰይፉ አጠናቀቀው።
~> ሳዳም ለአንገት ገመድ ሲሳይ ሆነ።
~> ቢን ዐሊ ሀገሩን ጥሎ ስደት ገባ።
~> ጋዳፊ ቱቦ ውስጥ ተጥሎ ተገኘ።

የደጋግ ሰዎች መቋጫ!
~~~~~~~~~~~~

⏩የነብዩ ዩሱፍ (ዐ•ሰ) ታሪክ በልጅነታቸው ያዩት ህልም እውን በመሆን ተጠናቀቀ።
⏩የነብዩ ሙሀመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ራዕይ መካን በድል በመግባትና እስልምናን የበላይ በማድረግ ተጠናቀቀ።

⏩ የነብዩ ዒሳ ( ዐ•ሰ) ተልዕኮ ወደ ሰማይ በማረግና ከፍ በመደረግ ተጠናቀቀ።
⏩ የሀምዛ (ረ•ዐ) ታሪክ በአላህ መንገድ ላይ ሸሂድ /መስዋእት በመሆን ተጠናቀቀ።
አላህ ፍፃሜያችንን ያሳምርልን።

6 - 0

አዩቲ wollo media 1⃣
Posted 5 days ago

፣ የፅናት ተምሳሌቷ እመት ዓኢሻ (ረ'ዐ )💙

ከሚገርሙኝ የሕይወት ታሪኮች መካከል አንዱ የእናታችን የነብዩ (ሶ ዐ ወ )የእመተ ዓኢሻ ( ረ ዐ. )ታሪክ ነው።
በ13 አመቷ ነበር ያገባችው ። ገና 18 አመቷ ነብዩ ( ሶ ዐ ወ ) ተለዩዋት። የሚወዷትና የምትወዳቸው ባለቤታቸው ወደ አኺራ ተሻገሩ።
አስር ዓመት እንኮን ከነብዩ ( ሶ ዐ ወ ) ጋር አልኖረችም።
አዎ ዓኢሻ ( ረ ዐ ) ገና በአፍላ ወጣትነቷ ያውም በእጅጉ የምትወዳቸውን ተወዳጅ ባለቤቷን ያጣችው ። በትዳር ዘመኗ ልጅ አልወለደችም ። የሚገርመው ልጅ ይኖረኝ ዘንድ ዱዓ አድርጉልኝ ብላ ነቢዩን ( ሶ ዐ ወ ) ጠይቃለች የሚል ሀድስ አልተገኝም ።
ከርሳቸው ህልፈት በሖላ ሌላ ሰው ሳታገባ 47 ዓመታትን ብቻዋን ኖረች። ዓኢሻ ( ረ ዐ ) ልጅ. ባይኖራትም ኡሙ ዐብደላህ. የዐብደላህ እናት በመባል ትጠራ ነበር።
እናት ዐኢሻ ( ረ ዐ ) ትልቁ ትኩረቷ መንፈሳዊ ነበር። ስለ. አለማዊ ሕይወት ግድ አልነበራትም ። በአላህ ክፍፍል ቅር አላላትም ። ሙሉ ሕይወቷ በዒባዳ፣ በዕውቀትና በጂሀድ የተሞላ ነበር ። ትላልቅ ሶሐቦች ጭምር ከሷ የድን ትምሕርት ተምረዋል ።ሃይማኖታዊ ጥያቄዎችን (ፈትዋ ) ለታላላቅ ሊቃውንት ታስረዳ ነበር ።

እህቴ እስቲ አስተዊ ከእመተ ዐኢሻ (ረ ዐ ) ሕይወት ብዙ ብዙ ነገር ትማሪያለሽ።
መከልከል በደል ቢሆን ኖሮ የነብዩ (ሶ ዐ ወ. )ሚስት የሆነችው ዐኢሻ ( ረ ዐ ) ልጅ የሌላት በመሆኑ ተበድላለች ማለት እንችል ነበር ። ግን. አይደለም ። አላህ ፍትሐዊና ምክንያታዊ የሆነ ጌታ ነው ። ነገሮችን ለምን አላማ እዳደረገ እሱ ያውቃል ። አላህ ሰወችን ምድር ላይ እሱ ባሻው መልኩ ሊያኖራቸው ይችላል ። ወደ ዱንአ ባዶ እጃቸውን መተው ባዶ እጃቸውን የሚመለሱ ብዙ ናቸው።
ታዲያ ከነዚያ ብዙ ሰዎች መካከል አንዱ ብንሆን ሊገርመን አይገባም።
ዱንያ የፈተና ምድር መሆኗ ግልፅ ነው። ለማንም አላዳላችም። ልጅ ስለጠፋ ፣ ትዳር ስለጠፋ ፣ ቤት ስለጠፋ፣ መኪና ስለጠፋ ፣ ገንዘብ ስለጠፋ ፣ ሕይወት አትቆምም ። ትቀጥላለች ።
አላህ በደለን ለሸይጧን መጥፎ ሀሳብና ጥርጣሬ በር አትስጡ ። መግቢያ ቀዳዳዎችን አትክፈቱ ።ከዚያ ይልቅ ቀልባችሁን አረጋጉ ። አላህ በሚወደው ነገር ላይ አተኩሩ።
እርሱ ለሚወደው ነገር ትኩረት. ስጡ ። ሁሉንም የሚሰጥ አላህ ነው።

Abx
(ሶባህል ኽይር )
የተወሰደ ገፅ _82 🤗

4 - 0