ይህ የዩቱብ ቻናል በመንፈሳዊ ሕይወት ላይ የሚያተኩር ይሆናል።
ስለዚህ በቻናሉ ላይ ስብከቶች ዝማሬዎች ቃለ መጠይቆች ወጎች እና የመሳሰሉት ይቀርቡበታል።
የቻናሉ ራዕይ
በ2018 ሁሉም አገልጋዮችና ተገልጋዮች በሃይማኖታቸው የቆሙ ሆነው ማየት፡፡
የቻናሉ ተልዕኮ
የተሟላና ስርዓት ያለው ለመፈፀም ቀልጣፋና ብቃት ያለው አገልግሎት በመዘርጋት ሁሉን አቀፍ አገልግሎት እንዲደርስ እና ቀጣይነት ባለው መልኩ መድረሱን ማረጋገጥ፡፡
የየቻናሉ እሴቶች
ታማኝነት፡- የመንፈሳዊ ቻናሉ የተመሠረተበትን ዓላማ ማሳካት እንዲችል በትጋት ማገልገልና በቅንነት መስራት፤
ተጠያቂነት፡- መንፈሳዊ ቻናሉ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንፆ ሃይማኖቱን የሚያውቅ ትውልድ እንዲበዛ ተግቶ የሚሠራ እንዲሆን ማድረግ
አሳታፊነት፡- መምህራነ ወንጌልንና ዘማርያንን በመንፈሳዊ ቻናሉ በመጋበዝ አገልግሎት እንዲሰጡና አስተዋፅኦ ማድረግ እንዲችሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፤
ግልፅነት፡- የሚጋበዙ እንግዶችን ቀድሞ በየጊዜ ለተከታታዮች ማሳወቅ፤
የቻናሉ ዓላማ
መንፈሳዊ አገልግሎት ለሁሉም እንዲዳረስ ማድረግ ነው
አገልግሎቱን ለማስፍት ሰብስክራይብ ሼር ላይክ በማድረግ አገልግሎቱን ያስፉ