Channel Avatar

Manyazewal Eshetu @UCkJ7RzEWXZsiM2dL0aQVifw@youtube.com

461K subscribers - no pronouns :c

Welcome to Manyazewal Eshetu Experience the best podcast in


Welcoem to posts!!

in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c

Manyazewal Eshetu
Posted 1 week ago

እጅግ በጣም ጠለቅ ያለ እውቀት የሚሰጥ ፖድካስት

8 - 0

Manyazewal Eshetu
Posted 1 week ago

እንጀራ ይስጣችሁ!

ያላሰባችሁትን በርከት ከቤታችሁ ያምጣው::

የገንዘብ ስጋታችሁን ከህይወታችሁ ይንቀለው::

ስኬት የእግዚአብሔር በረከት ነው::

ለብቻ ብንሮጥ ያገኘነው ሮጦ የሚሄድ ነው::

ትንሹ የአምላክ ፀጋ ለብዙ ይተርፋል::

ለብዙ የሚተርፈው አምላክ ለብዙ ተራፊ ያድርጋችሁ::

ከራሳችሁ አልፋችሁ ለሰው የምትደርሱ ያድርጋችሁ::
አሜን በሉ!

6.5K - 356

Manyazewal Eshetu
Posted 2 weeks ago

‪@comedianeshetu‬ በአሜሪካ የኮሜዲ ስራውን ያቀርባል::አእምሯችሁን በሳቅ እርፍ ማድረግ ከፈለጋችሁ አያምልጣችሁ::

መልካም እድል እሼ ወንድሜ

1.7K - 28

Manyazewal Eshetu
Posted 1 month ago

‪@itsyidi‬ ቃለመጠየቅ

20 - 5

Manyazewal Eshetu
Posted 1 month ago

በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ
የልብህን መሻት ይሰጥሃል!

መዝሙር 37:4

ግን በእግዚአብሔር ደስ
ብሎሃል? ብሎሻል?

5.9K - 153

Manyazewal Eshetu
Posted 1 month ago

ሁሉም ሰው የሚወደው
ጠባቂ መልዓክ አለው::

የእኔም ቅዱስ ገብርኤል ነው::

ማንም በሌለበት
ምንም በማላውቅበት ጊዜ አብሳሪው መልዓክ አግዞኛል::

ከጌታዬ ከኢየሱስ ክርስቶስ የህይወት መስመር እንዳልወጣ ረድቶኛል::

በተለይ በአርባምንጩ ቅዱስ ገብርኤል እንደማደጌ ታህሳስ 19ኝን ሳስብ ይነዝረኛል!

እንኳን አደረሰን!!

የእናንተ ጠባቂ መልዓክ ማን ነው?

ዛሬን የት አከበራችሁ?

መልካም በዓል

6.1K - 136

Manyazewal Eshetu
Posted 1 month ago

ይህ ህይወት ቀያሪ ቪዲዮ ነው!

46 - 0

Manyazewal Eshetu
Posted 1 month ago

አሁን እንደዚህ ያለ ቪዲዮ በነፃ ይገኛል?
አይታችሁ መስክሩ!

ሁለተኛ ቻነላችንን subscribe አድርጉ!!
👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/gVYUk9-hHHA?si=ROQKw...

73 - 0

Manyazewal Eshetu
Posted 2 months ago

ከንቱ ኩራትን ምን አመጣው?
ሟች መሆንሽ ተረሳ?

ምክንያትሽ ምንድን ነው?

ሰው ነሽና ሰው የማይረዳው ምክንያት አታጪም::

የምድር ህይወት መሰቃየት ነው::

የልጅነት የዋነት ተሰርቀሻል::
የአምላክ ፍቅርን ክደሽ በቁስ ፍቅር ተጠምቀሻል::

ባርነት ነው::ነፍስን አጥቶ አለምን ማግኘት ታላቅ ክስረት ነው::

ፊትሽ ይስቃል::አለባበስሽ ያንፀባርቃል::

ሰው ሁሉ አንቺን መሆን ሲመኝ ያአንቺ ውስጥ ግን ሞትን ይመኛል::

ምንድን ነው ግን ህይወት?
ምንድን ነው ግን የመኖር መጨረሻው?

ሞት?

ሞት አለ::
ሁሉን በዜሮ ያበዛል::
ከአፈር ጋር ይደምራል::

ታዲያ በምድር ቁስ መሰብሰቡ ሞትን ካላሸነፈ ምን ይሰራል?

ሞትን የሚያሸንፍ አንድ ነገር የነፍስሽ መንቃት ነው::

ነፍስ ስጋዊ ምኞትን ጥሳ መንፈሳዊ ውበቷን ስታገኝ የህይወት ብርሃን ወደ ህይወትሽ ይፈሳል::

ማንም የማያውቃቸው ልባዊ ህመሞች : በር ዘግተሽ ያፈሰስሻቸው እንባዎች ትክክለኛ መድህኒት ያገኛሉ::

ለምን እኖራለው? የሚለው አሰልቺ ጥያቄ አምላክን ስታገኚ ይቆማል::

ከንቱ የሆነው ህይወትሽ በአምላክሽ ብርሃን ትርጉም ያገኛል::

የፈጠረሽ አምላክ ባንቺ በኩል ወደ አለም ይመጣል::

ለሀሳብሽ ብርሃን ..ለስራሽ መንፈሳዊ ሐይል ..እና ..ለስኬትሽ በረከት ይችራል::

አላማሽ አላማውሲሆን
በትንሿ ልጁ ትልቁ አምላክ ይከብራል::

የመዳኛሽ ሰዓቱ አሁን ነው::

አንቺ ሺ ጊዜ ብታጠፊ እሱ ቢሊዬን ጊዜ ይረዳሻል::

ቢሊዬን ጊዜ ብትሳሳቺ ደግሞ ለዓለመ ዓለም ይጠብቅሻል::

ለከንቱ አለም ብለሽ ህያው አምላክሽን አታስጠብቂው::

አሁን ልብሽን ወደ አምላክሽ አድርጊ::

አሁን ወስኚ.........

አለም ይሻልሻል ወይስ አምላክ?

2K - 44

Manyazewal Eshetu
Posted 2 months ago

በ16ኛው ዙር የአርባምንጩ ሪትሪት ላይ
ተሳተፉ
ከታህሳስ 4 እስከ 7
በ0987209020 ይደውሉ
አሁን ይመዝገቡ

330 - 4