in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c
"ጾምን የምንጾመው ዲያብሎስንና ግብረ ኃጢአትን ለማሸነፍ ነው::" ቅዱስነታቸው
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ2017 ዓ.ም የዐቢይ ጾምን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ !
የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም
ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው መነሻ <<ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ ከተጠመቀ በኋላ ሳይውል ሳያድር ወዲያውኑ ወደ በረኻ በመሄድ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾመ፡፡>> በማለት የጌታችንና አምላካችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጾሙን ጥንተ ነገር አውስተዋል።
ቅዱስነታቸው በአርባ ቀናት ውስጥ የጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በዲያቢሎስ መፈተንና ድል መንሳትም አብራርተው ሲያወሱ <<በዚህ ጊዜ የጌታችን መልስ “ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ ኣይኖርም” የሚል ነበረ፤
ጌታችን በዚህ አባባሉ የዲያብሎስን ክፉ ሐሳብ የሚንድ እንጂ የእሱ ታዛዥ አለመሆኑን ኣሳየ፤ ዲያብሎስ በዚህ ሳያበቃ በትዕቢት በፍቅረ ንዋይና በባዕድ አምልኮ ሊጥለው ደጋግሞ ሙከራ አደረገ፤ ግን አልተሳካለትም፤>> ብለዋል።
ቅዱስነታቸው የመጾማችንን ምክንያት ሲያጠይቁ <<...የዲያብሎስን ፈተናዎች እንዴት በድል ማለፍ እንደምንችል ጌታችን በተግባር ኣሳይቶናል፤ ጌታችን ዲያብሎስን ያሸነበፈበት ስልት በመንፈስ ልዕልና እንጂ በዱላም፣ በካባድ መሳሪያም ኣይደለም፤ አለመሆኑንም የድርጊቱ ሂደት በግልጽ ያመለክታል፤ እንግዲያውስ እኛም ዲያብሎስን የምናሸንፈው በዚህ የመንፈስ ልዕልና ነው ማለት ነው::... ስለሆነም ጾምን የምንጾመው በዚህ ስልት ዲያብሎስንና ግብረ ኃጢአትን ለማሸነፍ ነው::
ከዚህ አኳያ ዲያብሎስን ለማሸነፍ መጾም ግድ ስለሆነ ጌታችን በከፈተልንና ባሳየን መንገድ እንጾማለን>> ብለዋል።
ስንጾምም <<የምንጾመው መልካም ኅሊና ኖሮን ለእግዚአብሔር ለመታዘዝና ለመገዛት፣ ከዚያም ከቃሉ በተነገረን መሠረት የተራቡትን ልንመግብ፣ የተራቈቱትን ልናለብስ፣ የተጣሉትን ልናስታርቅ፣ ፍትሕ ያጡትን ፍትሕ እንዲያገኙ ልናደርግ፣ ለንኡሳን የሕብረተ ሰብ ክፍሎች የተለየ ትኵረት ልንሰጥ፤ እኩልና ፍትሓዊ የሀብት ክፍፍል በሰው ልጆች መካከል ልናረጋግጥ፣ ሰብኣዊ ክብር እንዳይነካ ጦርነት፣ ጥላቻ፣ አደገኛ የቃላት ውርወራና መነቃቀፍ እንዲቀር ልናደርግ ነው፤>> በማለት አጽንዖት ሰጥተው አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
3 - 0
ቃና ዘገሊላ
በቃና ዘገሊላ ወይም በገሊላዋ ቃና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የፈጸመውን ተአምር በማሰብ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በዓል ታከብራለች፡፡ ይህም በጥምቀት በዓል ማግስት በጥር ፲፪ ነው፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ክፍል በምትሆን በቃና በተደረገ ሰርግ ላይ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ተገኝቶ ነበር፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም በወንጌሉ ‹‹የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ድንግል ማርያምም በዚያ ነበረች›› እንዳለ እመቤታችን ለሠርገኞቹ ዘመድ ነበረችና ከልጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ በሠርጉ ላይ ተገኝታ ነበር፡፡ በተጨማሪ ደግሞ ደቀ መዛሙርቱ ከጌታ ጋር በሠርጉ ተገኝተው ነበር፡፡ ሆኖም ግን የሠርጉ ሥነ ሥርዓት እየተከናወነ ባለበት ጊዜ ድንገት የወይን ጠጅ አለቀ፡፡ አሳላፊዎቹም በጭንቀት ግራ በገባቸው ጊዜ የጭንቅ አማላጅ አዛኝ እናታችን ድንግል ማርያም ጭንቀታቸውን ተረድታ ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘወር ብላ ‹‹የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም›› አለችው፡፡
እርሱም መልሶ ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› ‹‹ጊዜዬ ገና አልደረሰም›› አላት፡፡ እመቤታችንም ለአሳላፊዎቹ ‹‹የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ›› አለቻቸው፡፡ ጌታም በቦታው የነበሩ ስድስት የድንጋይ ጋኖች ውኃ ሞልተው እንዲያመጡ አዘዛቸው፡፡ ሲያመጡለትም ውኃውንም ወደ ወይን ለውጦ ለአሳዳሪው እንዲሠጡት አዘዘ፡፡ አሳዳሪውም ወደ ወይን የተለወጠውን ውኃ በቀመሰ ጊዜ አደነቀ፡፡ ከወዴት እንደመጣ ስላላወቀ ሙሽራውን ‹‹ሰው ሁሉ መልካሙን የወይን ጠጅ አስቀድሞ ያመጣል፤ ከጠገቡ በኋላም ተርታውን ያመጣል፤ አንተ ግን መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆየህ›› አለው፡፡ (ዮሐ.፪፥፩-፲፩)
ይህንን ድንቅ ተአምርም በማሰብ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን አስተምህሮ በጥምቀት በዓል ማግስት ቀን የቃና ዘገሊላ በዓል ይከበራል፡፡ የቃና ዘገሊላ ጥንተ ነገሩ የተፈጸመው የካቲት ፳፫ ቀን ነው፡፡ ነገር ግን አባቶቻችን የውኃን በዓል ከውኃ በዓል ጋር ለማክበር ብለው የካቲቱን በዓል ወደ ጥር ፲፪ አምጥተውታል፡፡ ይህም ውኃ ወደ ወይን የተለወጠበትን በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ለማከናወን ነው፡፡
ከበዓሉ ረድኤት ያሳትፈን፤ አሜን!
12 - 0
ዜና ዕረፍት
"አባ ወርቅነህ ተሰማ"
የበገናው አባት አባ ወርቅነህ ተሰማ ፤ የታላቁ በገነኛ የአለቃ ተሰማ ወልደ አማኑኤል ልጅ በትናንትናው እለት በታህሳስ ፳፫ በቅዱስ ዳዊት አመታዊ በዓለ እረፍት ቀን እርሳቸውም ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል።
አረጋዊው አባት አባ ወርቅነህ ተሰማ ከወጣትነት እድሜያቸው ጀምሮ እስከ እረፍታቸው ድረስ ጸሎተኛ ፣ እንደ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እና እንደአባቶቻቸው ሁሉ እግዚአብሔርን በበገና የሚያመሰግኑ በገነኛ፣ መዝሙረኛም ነበሩ።
ቀብራቸው ዛሬ ከቀኑ 9:00 ላይ በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ቤተ ክርስቲያን ይከናወናል።
-የአባታችንን ነፍስ በአጸደ ገነት ያኑርልን!
3 - 0
Qnie tube ቅኔ ቲዩብ
እንኳን ወደ ቅኔ ቲዩብ በሰላም መጡ በዚህ ቻናል የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ወቅታዊ የቤተክርስቲያን መረጃዎች፣ገዳማት አድባራት እና መዝሙሮች እንዲሁም የመንፈሳዊ መጻሕፍት ዳሰሳዎች ፣ አጫጭር የቤተ-ክርስቲያን ዶክመንታሪዎች እና ዝማሬዎች ይቀርቡበታል፡፡የቻናሉን ይዘቶች ለሌሎች ያጋሩ እናመሰኛለን ፡፡