Channel Avatar

ማኅቶተ ዘመን ሚድያ @UCXXJLlaQcQ4eNxoc-fRf-Aw@youtube.com

1.2K subscribers - no pronouns :c

ማኅቶተ ዘመን ሚድያ Mahtote Zemen MediaTube ኦርቶዶክሳዊ የቪድዮ ትምህርቶች፣ መ


Welcoem to posts!!

in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c

ማኅቶተ ዘመን ሚድያ
Posted 1 month ago

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ 


ልዑል እግዚአብሔር በክቡር ደሙ የዋጃችሁ የእግዚአብሔር ልጆች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የመስቀል ሥር የበረከትና የአደራ ልጆች የጻድቃን ወዳጆች ምእመናንና ምእመናት በያላችሁበት ቦታ ሁሉ እንኳን ለ2017 ዓ-ም ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት (ለብርሃነ ልደቱ) በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን 


 የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ሰውና መላእክት አንድ ሆነው ተስማምተው በቤተ ልሔም ዝማሬ ያቀረቡበት ሰማይና ምድር የታረቁበት ሰውና እግዚአብሔር ሕዝብና አሕዛብ ነፍስና ሥጋ የተስማሙበት ፍጹም ትሕትና የተሰበከበት 

ከጨለማና ከሞት እሥራት ዓለሙን ሁሉ ይፈታው ዘንድ የክብር ሁሉ ባለቤት የዓለም መድኃኒት የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ አምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ ብሎ ለአዳም በገባው ቃል መሠረት ከሰዓቱ አንድ ሰዓት ከዕለቱ አንድ ዕለት ከወሩ አንድ ወር ከዓመቱ አንድ ዓመት ሳያዛንፍ ሳያተርፍ ሳይጨምር ሳይቀንስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በቤተ ልሔም በተወለደ ጊዜ መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ ለነበሩ እረኞች ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ሉቃ ፪÷፲ (2÷10) በማለት በመልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ታላቅ ደስታ የተነገረበት ዕለት ሲሆን አስቀድሞ ደስታ የራቀው በፍርሃት የራደ በኃጢአት የደቀቀ መርገመ አዳም የወደቀበት 5,500 ዘመን በኃጢአት በሽታ ተይዞ የነበረ መድኃኒት ያጣ ሕመምተኛ በጨለማ የሚኖር በዲያብሎስ የአገዛዝ ቀንበር ሥር  ወድቆ በምርኮ በባርነት በስደት በመከራ የሚኖር ነጻነት የሌለው ኃዘን መከራ የጸናበት መጠጊያ የሌለው ለኃጢአት ባሪያ ሆኖ ሲገዛ የኖረ ሕዝብ የመከራውና የሞቱ ደብዳቤ ሲቀደድ ፋይሉ ሲዘጋ 

በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ በሞት ጥላ ሀገር ለሚኖሩ ብርሃን ወጣላቸው ተብሎ የተዘመረለት ሕዝብ ልጆች ናቸውና ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ በማለት በኃጢአት በሽታ ተይዞ የነበረ ዓለም መድኃኒት ያስፈልገዋልና ጨለማውን የሚያርቅ እውነተኛ ብርሃን በዳዊት ከተማ የዓለም መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ እንደ ተወለደ ለ5,500 ዘመን የነበረው የዲያብሎስ አገዛዝና የጨለማው ጉዞ መወገዱን በታላቅ ደስታ አበሠራቸው ለእኛም በዚህ ዘመን ለምንኖር እግዚአብሔር አምላክ ምሕረቱ የማያልቅ ቸርነቱ የበዛ እንዲታረቀን ይቅርም እንዲለን

በዚህ ዘመን በመከራ በስደት በጦርነት በስቃይ በሕመም በረኃብ የሚሰቃየውን ሕዝብ እያሰብን በዓሉን እንድናከብር እግዚአብሔር አምላክ ይርዳን

 በዓሉ የሰላም የበረከት የአንድነት የበጎነት ይሁንልን

 

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን 

2 - 1

ማኅቶተ ዘመን ሚድያ
Posted 4 months ago

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ 

እንኳን ለወርኃ ጽጌ አደረሳችሁ ከመስከረም 26እስከ ኅዳር 6 ወርኃ ጽጌ ይባላል ወርኃ ጽጌ እመቤታችን ድንግል ማርያም ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ወደ ምድረ ግብጽ የተሰደደችበትን መከራዋን የደረሰባትን መከራና ኃዘን ረኃብና ጥም በማሰብ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ክበበ ጌራ ወርቅ እያሉ በደማቅ ማኅሌት ምእመናን ሊቃውንቱን ከበው በእልልታ በጭብጨባ ሲያመሰግኑ የሚያድሩበትና

በሌላ መልኩ ደግሞ መዓዛው የሚጣፍጥ ለአይን የሚማርክ አበባ በድር ላይ ፍክት ብሎ የሚታይበት ወቅት ሲሆን አበባን ተወዳጅ የሚያደርገው ማራኪ የሆነው ውጫዊ ገጽታው ብቻ ሳይሆን ለሰውም ለእንስሳትም ሕይወት በተስፋነት የሚጠበቀው ፍሬ መገኛ ስለሆነ ጭምር ነው ጽጌ የእመቤታችን ምሳሌ  ነው ምሳሌ መሆኑም  እውነተኛው ፍሬ ክርስቶስ ከእርሷ መገኘቱን ለማመልከት ሲሆን  ትውልድ ሁሉ ለዘለዓለም ያመሰግናታል መዓዛ ቅዱሳን ምዕራገ ጸሎት ስለሆነች ጸሎቷ ልመናዋ በረከቷ አማላጅነቷ በሁላችን ላይ አድሮና ጸንቶ ይኑር አሜን 

12 - 0

ማኅቶተ ዘመን ሚድያ
Posted 4 months ago

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

“የመስቀል ዕንቅፋት ተወግዶአል።”
ገላ.፭፥፲፩

በሀገር ውስጥ እና በውጩ ዓለም የምትኖሩ የተከበራችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች ምእመናንና ምእመናት!

በቅድሚያ እንኳን እግዚአብሔር ለ ፳፻፲፯ ዓ.ም በዓለ መስቀል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን!

የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች! 

ጥላቻ የክርስቲያኖች መገለጫ ባሕርይ አይደለምና ጌታ ሰላምንና ዕርቅን ያደርግ ዘንድ ጥልን በመስቀሉ ገደለ።
ኤፌ.፪ ፥፲፭-፲፮

በዚህም ጌታ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ባሳየን የፍቅር ጥግ ባደረገልንም ዕርቅ እና ሰላም ምክንያት፤
መስቀሉ፦
የሰላም፣
የፍቅርና
የዕርቅ ምልክት ሆነ።

በዚህ የሰላም ምልክት በሆነው ቅዱስ መስቀል ታዲያ ብዙዎቹ ከሕመማቸው እየተፈወሱ ሰላምን ያገኙ ነበር።

ነገር ግን ይህ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መስቀል፦
ሙታንን እያነሣ፣
ለምጻሙን እያነፃ፣
ጎባጣውን እያቀና፣
ሕሙማንን እየፈወሰ፣
ተአምራትን ሲሠራ ይህ እውነት ያልተዋጠላቸው አይሁድ በመስቀሉ ላይ የተገለጠውን የእግዘብሔርን መለኮታዊ  ሥራ ቀብረው ለመደበቅ ሰይጣናዊ አሳብ በልባቸው ገባ።

ስለዚህ መስቀሉን ቀብረው ከሦስት መቶ ዓመታት በላይ ተራራ ሆኖ ገዝፎ እስኪታይ ድረስ ከአከባቢያቸው ያለውን ቆሻሻ እና የቤታቸውን ጥራጊ ወስደው ደፉበት።

ዛሬም በዚህ መንገድ እውነትን በማይሹ ወገኖች ለሀገር በረከት የሆኑ በርካታ እውነቶች እንዲህ ይቀበራሉ።

ነገር ግን እግዚአብሔር ሥራውን የሚሠራበት የእግዚአብሔር የሥራ ጊዜ ሲደርስ እነ ኪራኮስ እውነት ያለችበትን ሥፍራ መደበቅ አይችሉም።

ምክንያቱም ለሀገርና ለወገን የሚጠቅሙ በርካታ የተደበቁ እውነቶችን ፈልፍለው የሚያወጡ እነ እሌኒን በጊዜው ጊዜ እግዚአብሔር ይቀሰቅሳልና። 

ቅዱሱ መስቀል ከተቀበረበት ሥፍራ የተገኘበትን በዓል ስናከብርም እውነቱ ሁሉ ይህ ነው።

እግዚአብሔር መስቀሉን ከተቀበረበት ሥፍራ እንድታወጣ ለዚህ ታሪካዊ እና መንፈሳዊ ዓላማ ያዘጋጃት ንግሥት እሌኒ በሰጠችው መመሪያ መሠረት፦
ደመራ ተደምሮ፤
በእሳት ተለኩሶ፤
ሰንድሮስ የተባለ ብዙ ዕጣን ተጨምሮበት የዕጣኑ ጢስ የጌታ መስቀል ከተቀበረበት ሥፍራ ጎልጎታ ላይ ሄዶ አረፈ።

"ሰገደ ጢስ በጎልጎታ" እንዳለ ሊቁ።

ደመራው ተለኩሶ የዕጣኑ ጢስ ካረፈበት ቦታ ላይ መስቀሉ ያለበት ስፍራ ተገኝቶአልና መስከረም ፲፯ ቀን ቁፋሮ ተጀምሮ መጋቢት ፲ ቀን ቅዱሱ መስቀል እንደ ፀሐይ እያበራ ከተቀበረበት ሥፍራ ወጣ።

በደዌ እሥራት የነበሩ በርካታ ሕሙማንም በመስቀሉ ላይ በተገለጠው በእግዚአብሔር መለኮታዊ ኃይል ከሕመማቸው ተፈወሱ።

እንዲህ የሚፈውሰውን ቅዱሱን መስቀል ለፈዉስ ያልታደለው የአይሁድ ሕዝብ ተባብሮ ቀበረው።

ነገር ግን በእግዚአብሔር ድንቅ ጥበብ የመስቀሉ እንቅፋት ተወግዶ
መስቀሉ ወደ አደባባይ ወጣ።
ወደ ኢትዮጵያም መጣ።

እኛም ዛሬ ለሰላማችን እና ለአንድነታችን እንቅፋት የሆኑብንን ነገሮች እግዚአብሔር እንዲያስወግድልን እውነትን ተባብረው የሚቀብሩ አይሁድን ሳይሆን
ትውልድ የሚፈወስበትን እውነት ቆፍረው የሚያወጡ እነ እሌኒን ልንሆን ይገባል።

የተወደዳችሁ ክርስቲያኖች!
“የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።”
፩ቆሮ. ፩፥ ፲፰
በዓሉን ስናከብር ኃይልን በሚሰጠን በክርስቶስ
የታረዙትን በማልበስ፤
የተራቡትን በማጉረስ፤
የተጠሙትን በማርካት፤
የተቸገሩትን በመርዳት መሆን እንዳለበት በእግዚአብሔር ልዩ ፍቅር ልናሳስባችሁ እንወዳለን።

መስቀል፦
ክርስቶስ ፍቅሩን ለእኛ በተግባር ያሳየበት የፍቅር ምልክት ነውና በዓሉን ስናከብር  በፍቅር ሊሆን ይገባል።

መስቀል፦
ክርስቶስ ሰላምን ለሰው ልጆች የሰጠበት የሰላም አርማ፤
የሰላም ምልክት ነውና በዓሉን በሰላም እና ፍጹም በሆነ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ልናከብረው ይገባል።

መስቀል፦
ክርስቶስ እኛን ከራሱ ጋር ያስታረቀበት የዕርቅ ምልክት ነውና ከተጣሉን ሰዎች ጋር በመታረቅ በዓሉን ፍጹም በሆነ ዕርቅ በጋራ ልናከብር ይገባል።
ይህ የመስቀል ደመራ በዓል ከሃይማኖታዊ ይዘቱም ባሻገር በዩኔስኮ በዓለም አቀፍ የታሪክ መዝገብ ላይ ተመዝግቦ
የጋራ በዓላችን፤
የጋራ ታሪካችን፤
የጋራ ቅርሳችን፤
የጋራ ውበታችን፤
ነው
የእግዚአብሔር ቸርነቱ
የእመ ብርሃን ምልጃ በረከቷ
የቅዱሳን መላእክት ጥበቃ
የቅዱሳን አባቶቻችን ጸጋ እና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን!

ልዑል እግዚአብሔር
ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ሰላምን
ለዓለሙ ሁሉ ፍቅርን አንድነትን ይስጥልን! 

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ

9 - 0

ማኅቶተ ዘመን ሚድያ
Posted 5 months ago

አባ ጊዮርጊስ  ዘጋስጫ በሰዓታት ዘሌሊት ጸሎቱ  በነቢዩ በዳዊት ጸሎት እግዚአብሔርን ያመሰገነበት   

ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ እሥራኤል 


ብቻውን ድንቅ ተአምራትን ያደረገ የእሥራኤል አምላክ እግዚአብሔር  ይክብር ይመስገን።

የጌትነቱም ስም ይክበር ይመስገን። 

ምስጋናውም በምድር ሁሉ ላይ ይምላ።

 ይሁን ይሁን ይደረግ።

 አሸናፊ እግዚአብሔር  ሆይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ ትመሰገናለህ ምስጋናህም በምድር በሰማይ የመላ ነው ።

ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ለዘለዓለሙ የሚኖር እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብሎ ይመሰገናል። 

በትጉሃን መላእክት የሚመሰገን በቅዱሳንም የሚቀደስ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብሎ ይመሰገናል። 

ኪሮቤል የሚፈሩት ሱራፌልም ከግርማው የተነሣ የሚንቀጠቀጡለት እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ  ተብሎ ይመሰገናል። 

መብረቁን የሚመልሰው ነጎድጓዱንም የሚያጸናው እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ  ተብሎ ይመሰገናል። 

  በመሸ ጊዜ ጨለማውን የሚያመጣ ብርሃንንም ወደ ሰሜን የሚመልስ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ  ተብሎ ይመሰገናል።

በሰማይ ጠፈር ያበራልን ዘንድ ፀሐይን በቀን ያሰለጠነ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ  ተብሎ ይመሰገናል ። 

ጨረቃንና ከዋክብትን በሌሊት ያበሩ ዘንድ ያሰለጠናቸው እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ  ተብሎ ይመሰገናል።

 ሰማይን እንደ መጋረጃ የዘረጋ ምድርንም በውኃ ላይ ያጸና እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስቅዱስ ተብሎ ይመሰገናል ። 

አዳምን በእርሱ አርአያ በእርሱ አምሳል የፈጠረ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ  ተብሎ ይመሰገናል።

ከኖኅ ጋር ቃል ኪዳንን ያጸና እግዚአብሔር  ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ  ተብሎ ይመሰገናል።

ለአብርሃም ሕግን የሠራ ለይስሐቅም የማለ ለያዕቆብም አምልኮቱን ያጸና እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ  ተብሎ ይመሰገናል።

ለሕዝብ ምግብን ያድል ዘንድ ዘንድ ከዮሴፍ ጋር የተሸጠ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብሎ ይመሰገናል ።

 ለሙሴ ሕግን የሰጠ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ  ተብሎ ይመሰገናል ።

የአሮንን ክህነት ያከበረ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ  ተብሎ ይመሰገናል ። 

ዳዊትን የትንቢትና የመንግሥት ቅብዐትን የቀባው እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ  ተብሎ ይመሰገናል ።

 ለሕዝብ ቃሉን ያሰማ ዘንድ በነቢያት መንፈስን ያሳደረ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብሎ ይመሰገናል ።

መላእክት ሥልጣናት የሚያመሰግኑት እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብሎ ይመሰገናል ። እግዚአብሔርን አመስግኑት ስሙንም ጥሩ ። ለአሕዛብም ሥራውን ንገሯቸው እግዚአብሔር አመስገኑት ቸር ነውና ቸርነቱም ለዘለዓለም ነውና  የእሥራኤል ወገኖች እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ንገሩ ቸርነቱም ለዘለዓለም እንደ ሆነ ።

የአሮን ወገኖች እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ንገሩ ቸርነቱም ለዘለዓለም ነውና ።

እውነትን ፈራጅ እግዚአብሔርን አመስግኑ ቸርነቱ ለዘለዓለም ነውና ። 

ዓለምን የያዘ እግዚአብሔርን አመሰግኑ ቸርነቱ ለዘለዓለም ነውና የቅዱሳን ብርሃን እግዚአብሔርን አመስግኑ  ቸርነቱ ለዘለዓለም ነውና የደጋጎች ወዳጅ እግዚአብሔርን አመስገኑ ቸርነቱ ለዘለዓለም ነውና የአምላኮችን አምላክ እግዚአብሔርን አመስግኑ ቸርነቱ ለዘለዓለም ነውና የሰማይን አምላክ ። እግዚአብሔርን አመስገኑ ቸርነቱ ለዘለዓለም ነውና አቤቱ ቸርነትህን ለዘለዓለሙ አመስግናለሁ ። ስለቸርነትህና ስለፍርድህ እዘምርሃለሁ አቤቱ ለአንተ እገዛለሁ ቸርነትህና ጽድቅህ ሁል ጊዜ ያግኙኝ አቤቱ


 ለአንተ እገዛለሁ አቤቱ አንተ ቸር ይቅር ባይ ነህና ለአንተ እገዛለሁ መዓትህ የራቀ ቸርነትህ የበዛ እውነተኛ ነህና ።

አቤቱ ለአንተ እገዛለሁ አቤቱ በፍጹም ልቤ እገዛልሃለሁ ክብርህንም ሁሉ እናገራለሁ ።

አምላኬ ሆይ በፍጹም ልቤ እገዛልሃለሁ የአፌን ልመና ሁሉ ሰምተኸኛልና ለአንተ እገዛለሁ ።

አቤቱ ለአንተ አገዛለሁ እገዛልሃለሁ ስምህንም እጠራለሁ በአፌ ለእግዚአብሔር  ብዙ ምስጋናን አቀርባለሁ በብዙ ሕዝብ መካከልም አመሰግነዋለሁ


 ምስጋና  ይሁን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ በየጊዜውና በየሰዓቱ ሁሉ ። 


ምስጋና ይሁን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ በየዘመኑና በየዓመቱ ሁሉ ።


ምስጋና  ይሁን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ በተቀደሰች ቤተ ክርስቲያን ።

መቼም መች ለዘለዓለሙ በልጅ ልጅ ሁሉ ለእርሱ ሊሰገድለት ይገባል ።።።

16 - 1

ማኅቶተ ዘመን ሚድያ
Posted 5 months ago

በሰመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

 እንኳን ለጾመ ፍልሰታ የሱባኤ ወቅት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ይህ ጾም ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ሲሆን ጾሙንም የጀመሩት ቅዱሳን ሐዋርያት ናቸው ለእሱም መሠረታቸውም መነሻቸውም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዜና ዕረፍቷ ነው  መላ ዘመኗ 64 ሲሆን ከእናት ከአባቷ ቤት  ፫ ዓመት 
ከቤተ መቅደስ ፲፪ ዓመት 
በድምሩ 15 ዓመት ይሆናል ። 
ጌታን ጸንሳ ፱ ወር ከ፭  ቀን
 ከጌታ ልደት እስከ ስቅለቱ  33 ዓመት ከ3 ወር ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር 

 ቅዱስ ዮሐንስ በመስቀል ሥር አደራ ከተቀበላት በኋላ ደግሞ በቤተ ዮሐንስ 15 ዓመት ይህንን ቢደምሩት 64 ዓመት ይሆናል እመቤታችን 64 ዓመት ሲሆናት ጥር 21 በዕለተ እሑድ አርፋለች 

ሐዋርያት በአጎበር አድርገው ወደ ቤተ እግዚአብሔር ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና ቀድሞ ከዚች የተወለደውን ሞተ፣ ተነሣ ፣ዐረገ እያሉ ዓለሙን ሲያውኩት ኖሩ ደግሞ ዛሬ ይችን ሞተች፣ ተነሣች፣ ዐረገች እያሉ ይህን ዓለም ሲያውኩት ሊኖሩ አይደለምን ? ንዑ ናውዕያ በእሳት ኑ በእሳት እናቃጥላት ብለው  ተሰብስበው መጡ ከእነሱም መካከል ታውፋንያ የሚባል ጉልበተኛ ሰው ተረምዶ የአልጋውን ሸንኮር ያዘው  ያን ጊዜ መልአኩ በረቂቅ ሰይፍ እጁን ቀጥቶታል።
ከዚህ በኋላ መልአኩ እመቤታችንን ከዮሐንስ ጋር በደመና ነጥቆ ወስዶ በገነት ከዕፀ ሕይወት እግር አኑሯታል ። ያንንም ሰው ቅዱስ ጴጥሮስ ጸልዮ አድኖታል ሐዋርያትን የምንጠላቸው የምናሳድዳቸው እንዲህ እያደረጉን እንዳይሉ ምክንያት ለማሳጣት 

ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ሐዋርያት መጥቶ እመቤታችን በገነት ከዕፀ ሕይወት እግር አለች አላቸው እንዴት ዮሐንስ ዓይቶ እኛ ሳናይ እንቀራለን ብለው ነሐሴ አንድ ሰኞ ዕለት ሱባኤ ገቡ በ14ኛ ቀን እሑድ አምጥቶ ሰጥቷቸው ዕለቱን ቀብረዋት በሦስተኛው ቀን ማክሰኛ ዕለት ተነሥታለች።

 ያን ጊዜ ቶማስ አልነበረም ሀገረ ስብከቱ  ሕንደኬ ሄዶ ነበርና በደመና ተጭኖ ሲመጣ እመቤታችን ወደ ሰማይ ስታርግ መላእክት እመቤታችን እኮ ናት አትሰግድም እንዴ አለት ።

ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ ይላል ከደመናው  ሾልኮ  (ወልቆ) ሊወድቅ ወደደ ስለምን ቢሉ ተበሳጭቶ ቀድሞ ልጇ ጌታዬ ከትንሣኤው ለየኝ እሷም ከትንሣኤዋ ትለየኝን ? ብሎ ነው እመቤታችንም አይዞህ ይህንን ዕርገቴን ያየህ አንተ ብቻ ነህ እንጂ ሐዋርያት አላዩም እንካ ብላ የተገነዘችበትን ሰበኗን ሰጥታ ሰደደችው እርሱም መጥቶ ከሐዋርያት ጋር  ጥቂት ሲጨዋወት ቆይቶ የእመቤታችን ነገር እንዴት ሆነ አላቸው ሞታ ቀበርናት አሉት መቼ ሞተች? አላቸው በጥር አሉት መቼ ቀበራችኋት? አላቸው  በነሐሴ አሉት ሞት በጥር !  በነሐሴ መቃብር ! እንደምን ይሆናል ብሎ ዘበተባቸው

ቅዱስ ጴጥርስ አንተ ጥንቱንም መጠራጠር ልማድህ ነው  ቀድሞ የጌታን ትንሣኤ ብንነግርህ ካላየሁ አላምንም ብለህ እጅህ ከእሳት እንደጋባ ጅማት እርር ኩምትር ብሎ ነበር ደግሞ ዛሬ ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ እንዲሉ  አበው አጥበን ገንዘን የቀበርናት እኛ ሳለን አልሞተችም ትላለህን ? አሉት 

ምን አንተ ብቻ ተጠራጥረህ ትቀራለህ ሌላውንም ታጠራጥራለህ ብሎ ቅዱስ ጴጥሮስ መቆፈሪያውን ይዞ ወደ መቃብሩ ሄዱ ቢቆፍሩ አጧት ደነገጡ 

በዚህን ጊዜ ቅዱስ ቶማስ ለሐዋርያት እንዲህ አላቸው እናንተ እኔን አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ በዚያውም የምትሉትን ልስማ ብዬ ነው እንጂ እሷንማ ስታርግ አግኝቻታለሁ እንኩ ብሎ ሰበኗን ሰጣቸው እነሱም ተቀብለው እውነት ነው በዚህ ነው የገነዝናት ብለው አምናዋል ሰበኑንም ተካፍለው ወስደው ድውይ ሲፈውሱበት ሙት ሲያስነሱበት ኖረዋል ቶማስ ዓይቶ እንዴት እኛ ሳናይ እንቀራለን ብለው በዓመቱ ድጋሜ በነሐሴ አንድ ሱባኤ ገቡ በ16ኛው ቀን ጌታ ሠራዒ ካህን ቅዱስ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ እመቤታችንን መንበር አድርጎ ቀድሶ አቁርቧቸዋል 

ከዚህ በኋላ ለእመቤታችን ለዘጸውዐ ስመኪ ስምሽን የጠራውን ወለዘገብረ ተዝካረኪ መታሰቢያሽን ያደረገውን እምሕር ለኪ እምርልሻለሁ ብሎ 

ለቅዱሳን ሐዋርያት ለዘጸውዐ ስመክሙ ስማችሁን የጠራውን ወለዘገብረ ተዝካረክሙ መታሰቢያችሁን ያደረገውን እምሕር ለክሙ እምርላችኋለሁ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸው ተስፋውን ነግሯቸው ወደ ሰማይ አርጓል ። ጾመ ፍልሰታ በዚህ ምክንያት ተጀምሯል 

የእመቤታችን አማላጅነት የእግዚአብሔር ቸርነት አይለየን ። 

15 - 5

ማኅቶተ ዘመን ሚድያ
Posted 6 months ago

#ደብረ ታቦር
#ደብረ ታቦር ከዘጠኙ #ዐበይት በዓላት #አንዱ ነው #ደብር ተራራ #ታቦር የራራ ስም ነው ጌታ በመዋዕለ ስብከቱ ብዙውን ጊዜ የሚያስተምረው ተአምራት የሚያደርገው በተራራ ላይ ነበር #በዚህም ዕለት ከቅዱሳን ሐዋርያት ዘጠኙን ከእግረ ደብር ትቶ ሦስቱን ባለሟሎቹን #ጴጥሮስን #ዮሐንስንና #ያዕቆብን አስከትሎት ወደ ደብረ ታቦር ወጣ አስቀድሞ ጌታ በቂሣርያ ሳለ ደቀ መዛሙርቱን ስለራሱ ሰዎች የሰውን ልጅ #ማን እንደሆነ ይሉታል #ብሎ በጠየቀ ጊዜ ማቴ 16፥13 አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ ሌሎችም ኤልያስ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ብለውት ነበርና ።

እግዚአ ነቢያት እንደሆነ ለማጠየቅ። #ሙሴ የእኔን የሙሴን ጌታ ማን ሙሴ ይልሃል እግዚአ ሙሴ ይበሉህ እንጂ ሲል ኤልያስም የእኔን የኤልያስን ጌታ ማን ኤልያስ ነው ይልሃል እግዚአ ኤልያስ #ይበሉህ እንጂ ብለው ሲመሰክሩ ተሰምተዋል ። #ስለምን በተራራ አደረገው ቢሉ #ተራራ የወንጌል ምሳሌ ነው ተራራ ሲወጡት ያስቸግራል ያደክማል ከወጡት በኋላ ግን የቅርቡን የሩቁን ሲያሳይ ደስ ያሰኛልና #ወንጌልም ሲማሯት ታስቸግራለች ጹሙ ጸልዩ ስገዱ መጽውቱ ጠላትህን ውደድ ስትል ታስጨንቃለች ከተማሯት በኋላ ግን ጽድቅንና ኃጢአትን ክፉና በጎውን ለይታ ስለምታሳውቅ ደስ ታሰኛለችና #አንድም ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው ተራራ ሲውጡት በብዙ ጻዕር በብዙ ድካም እንደሆነ ሁሉ መንግሥተ ሰማያትም በብዙ መከራ ትወረሳለችና ስለምን ሁለቱን ሙሴንና ኤልያስን ከብሉይ ሦስቱን ከሐዋርያት ከሐዲስ አመጣ ቢሉ ተራራ በቤተ ክርስቲያን ስለሚመሰል በቤተ ክርስቲያን ብሉይም ሐዲስም እንዲነገሩ ለማጠየቅ ።#አንድም ከደናግል ኤልያስን ከመዓስባን ሙሴን አምጥቶ በቀኝ በግራ አቆማቸው ነቢያትም ሐዋርያትም ደናግልም መዓስባንም መንግሥተ ሰማያትን አንድ ሆነው እንደሚወርሷት ለማጠየቅ። በዚህ ጊዜ መኩ ተለውጦ ፊቱ እንደ ፀሐይ አብርቶ ልብሱ እንደ በረድ ነጽቶ ሙሴና ኤልያስ በቀኝና በግራው ሆነው ታዩአቸው #ቅዱስ ጴጥሮስ ቦታው ደስ ቤለው ጌታ ሆይ በዚህ መሆን ለእኛ መካም ነው ብትወድስ በዚህ ሦስት ዳስ #አንዱን ለአንተ #አንዱን ለሙሴ #አንዱን ለኤልያስ እንሥራ አለ እርሱም ገና ሲናገር እነሆ ብሩህ ደመና ጋረዳችው ። እንሆ ከደመናው በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት የሚል ድምጽ መጣ ደቀ መዛሙርቱ ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና ተነሡ አትፍሩም አላቸው አይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም ከትራራውም በወረዱ ጊዜ ኢየሱስ የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያያችሁትን ለማንም አትናገሩ ብሎ አዘዛቸው ።

9 - 1

ማኅቶተ ዘመን ሚድያ
Posted 6 months ago

#በስመ # አብ ወወልድ #ወመንፈስ ቅዱስ #አሐዱ አምላክ ።# የእግዚአብሔር #ቤተሰቦች #የእግዚአብሔር #ልጆች የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም #የመስቀል ሥር የአደራ ልጆች ነሐሴ ሰባት ቀን እመቤታችን የተጸነሰችበት ታላቅ በዓል ነው ከእመቤታችን ሠላሳ ሦስቱ በዓላት መካከል የመጀመሪያው ነው #በአዳም ምክንያት ሞት ዓለሙን ሁሉ ወደ ኃሣርና #ወደ ጨለማ ስለ ወሰደው እግዚአብሒር ለአዳም የገባለት ቃል ኪዳን የሰጠው ተስፋ በደረሰ ጊዜ 5,500 ዘመን ሊፈጸም 15 ዓመት ሲቀረው የሕይወት ፍሬ የሚገኝባት ዕፀ ሕይወት ረኃበ ነፍስን የሚያርቅ የሕይወትን ምግብ ያስገኘችልን ሕይወትን ድኅነትን የሚያድል ጽምዐ ነፍሳትን የሚያርቅ የሕይወት ምንጭ ኢየሱስ ክርስቶስ የተገኘባት ድንግል ማርያም #በቅድስት ሐና ማኅፀን ዛሬ ተጸነሰች ይህም እንዲህ ነው የእመቤታችን ቅድመ አያቶቿ ቴክታና በጥሪቃ ይባላሉ እጅግ ባለጠጋ ነብሩ ነገር ግን ልጅ ስላልነብራቸው አዘነው ተክዘው ሲኖሩ ሁል ጊዜ ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይተጉ ነበር የንጹሐንን ጸሎት የሚሰማ እግዚአብሔር ጸሎታቸውን ሰምቶ ቴክታ ፀነሰች ሔሜንን ወለዱ
#ሔሜን ዴርዴን ። ዴርዴ ቶናህን ።
#ቶናህ ሲካርን ። ሲካር ሔርሜላን ።
#ሔርሜላ ሐናን #ወለደች ።

#ቅድስት #ሐና ከነገደ #ይሁዳ የተወለደ ስሙ #ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው አግብታ ስትኖር እርሷም እንደ አያቶቿ መካን ሆነች ከዕለታት አንድ ቀን ከቤተ እግዚአብሔር ደርሳ እጅ ነሥታ ተሳልማ ስትመለስ #ርግቦች #ከዛፍ #ሥር #ከልጆቻቸው ጋር ሲጫወቱ አይታ አቤቱ ፈጣሪዬ ሁሉን ሁለት ሁለት አድርግህ ፈጥረኸዋል ለመሆኑ እኔን ባሪያህን ምን ብለህ ፈጥረኸኛል ? #ድንጊያ ብለህ ፈጥረኸኛል ? ለእንስሳቱ ለአእዋፋቱ ያልነሣኸውን ዘር ለእኔ ለምን ነሣኻኝ ? ብላ ምርር ብላ አለቀሰች ይህ ብቻ አይደለም ከዕለታት አንድ ቀን ከባለቤቷ ከኢያቄም ጋር መሥዋዕት ይዘው ወደ ቤተ #እግዜአብሔር ቢሄዱ መሥዋዕቱን የሚያሳርገው #ሊቀ ካህናቱ እናንተማ ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት ተብሎ
ለሰው የተነገረውን #ቃል ያስቀረባችሁ ርጉማን አይደላችሁምን ? ቢጠላችሁ ነው እንጂ ቢወዳችሁማ ልጅ ይሰጣችሁ አልነበረምን ?
#የኃጢአተኛውን መሥዋዕት እግዚአብሔር አይቀበልምና ምን አደክማችሁ አልቀበላችሁም ብሎ መሥዋዕታቸውን መለሰባችው በዚህም ምክንያት እያዘኑ እየተከዙ #ወደቤታቸው ሲመለሱ ይህ ሁሉ ተግዳሮትና ስድብን የምንሰማው ወደ እግዚአብሔር ተግተን ባናመክት አይደለምን ብለው ስእለት ተሳሉ #ሱባኤ #ገቡ በሱባያቸውም አቤቱ አምላካችን ስድባችንን ብታርቅልን ልጅም ብትሰጠን ወንድ ልጅ ከሆነ ወጥቶ ወርዶ አርሶ ቆፍሮ ነግዶ ያብላን ይርዳን አንልም ለቤተ እግዚአብሔር መብራት አብሪ መሥዋዕት አቅራቢ እንዲሆን ለአንተ እንሰጣለን ሴት ብንወልድ እንጨት ሰብራ #ቀድታ እንጀራ ጋግራ ምግብ አብስላ ትርዳን ትጡረን አንልም መሶበ #ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ እንድትኖር ለአንተ እንሰጣለን ብለው ብፅዓት ገቡ ። በራእይ ለእርሷ የብርሃን መቀነት ሲያስታጥቋት ለእርሱ የብርሃን መቋሚያ የብርሃን መነሳንስ ሲሰጡት አይታ ለባሏ ለኢያቄም ነገረችው እርሱም ከደጃቸው ዛፍ በቅላ ለምልማ አብባ አፍርታ ሰው ሁሉ ሲመገባት አየሁ አላት የሐናና የኢያቄም ጸሎታቸው #ቅድመ #እግዚአብሔር #ደረሰ ወዲያው #መልአኩ መጥቶ ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ ብሏቸው በብሥራተ መልአክ በፈቃደ እግዚአብሔር ነሐሴ ሰባት ቀን እመቤታችን #ቅድስት #ድንግል #ማርያም ተጸነሰች ለጊዜው ለእናት ለአባቷ #ጸጋ ሀብት ሆና ተሰጥታለች ፍጻሜው ግን ለሁላችንም ጸጋ ሀብት ሆና ስለተሰጠች የሰውን ጸሎት መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር የእግዚአብሔርን #ምሕረት #ቸርነት ወደ ሰው ታደርሳልች #ስለዚህ ለሁላችንም #ጸጋ ክብርን ከእግዚአብሔር ዘንድ ታሰጠናለች የእግዚአብሔር ቸርነት የእናታችን የቅድስት ድንግል #ማርያም ጸሎት #ልመና በረከት አማላጅነት አይለየን ጣዕሟ በአንደብታችን ፍቅሯ በልቡናችን #ለዘለዓለም #ጸንቶ #ይኑር ። # አሜን ።

10 - 2