Channel Avatar

መምህር ኢሳይያስ - memher esayiyas @UCUFuggW_5QpTY21qB7HIrAg@youtube.com

6.7K subscribers - no pronouns :c

Wellcome to memher esayiyas youtube channal


Welcoem to posts!!

in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c

መምህር ኢሳይያስ - memher esayiyas
Posted 1 month ago

ቡና ይጠጣል አይጠጣም?
በዚህ ዘመን እንደ ቡና አድርጎ ጉዳት ያደረሰብን ፍጡር የለም።እንዴት መሰላችሁ ቡና ሳይሆን ስለ ቡና የሚሰብኩ ሰዎች ናቸው የጎዱን።ለምን መሰላችሁ አምስቱ ውሾች ወደ መንግስተ ሰማያት አይገቡም ይላል መጻህፍ
★ነፍሰ ገዳዮች
★ስራይ የሚያደርጉት
★ሀሰተኞች
★ዘማውያን
★ጣኦት አምላክያን እነዚህ መንግስተ ሰማያት አይገቡም።ዋናዋናዎቹ ኃጥያቶች እነዚህ ናቸው። አውቆ ሰይጣን እነዚህን ኃጥያቶች ሰውን ሰው እያረደው ይሄ እንዳይሰበክ አድርጎ ስለነፍሰ ገዳይ እንዳይሰበክ አድርጎ ስለ አንድ የእንጨት ፍሬ እያከራከረ እንዴት እንደቀለድብን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ።ነፍስ መግደል እየተስፋፋ ክቡር የሰው ልጅ ዘማዊ ሆኖ ረክሶ ጎስቁሎ ከዝሙት ባርነት መውጣት አቅቶት መስሎ እየኖረ ነጭ ለብሶ ውስጡ ግን እንደ ቁራ ጠቁሮ እየኖረ ደም የከፈለለት የመድኃኔዓለም ልጅ ኃጥያት አስጎንብሶ ቀጥቅጦ እየገዛው ሰው አለ መሰላችሁ የለም እኮ የነቀዘ ነው እኮ በእውነቱ። መጽሐፍ ምን ይላል " ከአንበጣ የተረፈውን ትል በላው" ኢዮኤል ነው እንዲህ የሚለው አንበጣ የተባለው ክህደት ነው ምንፍቅና ነው ወይም ደግሞ መናፍቅ ሰራዊት ሀይማኖት የሌለው ሰራዊት ከአንበጣ የተረፈውን ትል በላው አለ ከክህደት እና ከጦርነት የተረፈውን ኃጥያት በላው ማለት ነው አሁን ብዙ በጦርነት ያልቃል ብዙዎቻችን ደግሞ ኃጥያት በልቶ ጨርሶናል።ላዩን ቀለም ተቀብቶ ውስጡን ሌባ እንደሰረቀው ቤት በሉት ዝም ብላችሁ። ውስጡ በኃጥያት ነኩሎ ፈርሶ ላዩ ግን ንጹህ ሆኖ የሚታይ ሰው እንደዛ ቤት ያለ ነው። ምንም ረብ ጥቅም የለውም! ከክርስቶስ ጋር አልተገናኘም ሰለዚህ መሰበክ ሲገባው ስለ ጥንቆላ ስለ ክህደት መሰበክ ሲገባው ክርስቶስን መስደብ እንደቀልድ እየታየ አብያተ ክርስቲያናትን ማቃጠል ሰው ማረድ እንደ ሽንኩርት መክተፍ ሲቀል እየታየ ይሄ መሰበክ ሲገባው በአንድ እንጨት ፍሬ እየተከራከሩ ቡና ይጠጣል?አይጠጣም? ይሄ ነው ጽድቁ? ስንት ክህደት እያለ ሥላሴን ሳናቅ ስለ ቡና እንከራከራለን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ምን ማለት ነው ብለን የምታምነውን አምላክ በትክክል ሳታቅ ስለ ቡና ጥያቄ መከራ ጻፍ ጻፍ ጻፍ ኧረ እንደው አይድረስ ነው። እንደው ባህታዊ ሦስት ወር ከመነነ ስብከት የሚጀምረው ቡና ነው። ቡና የጠጣችሁ ወዮላችሁ! ምነው የገደላችሁ ቢል? ምነው የዘሞታችሁ ቢል?ምነው ዘረኞች ወዮላችሁ ቢል ሀገር የምታፈርሱ ወዮላችሁ ቢል። አሁን እኔ ቡና ይጠጣልም አይጠጣም አላልኳችሁም ትልቁ ነገር ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ መስጠት ነው ። እንድንሰጥ እግዚአብሔር ይርዳን አሜን!

ቡና ማን የፈጠረው እንጨት ነው? እግዚአብሔር
እግዚአብሔር የፈጠረው ፍጥረት መልካም ነው አይደለም?ነው
እግዚአብሔር የረከሰ ፍጥረት ፈጥሯል?አልፈጠረም
ሰይጣን እራሱ ቅዱስ ፍጥረት አልነበረም እንዴ?ነው ማነው የበደለው? ራሱ ሰይጣን ነው

ታዲያ ቡና መልካም ፍጥረት ሆኖ ከተፈጠረ ምን አርጎ ነው የማይጠጣ ስንላቸው እንዲህ ይላሉ ፦

ሰይጣን መቋደሻየ ነው ብሏል ይላሉ! እንዴ?ሰይጣን እንግዲህ እንጀራ መቋደሻየ ነው ቢል በርሃብ ልናልቅ ነው እንዴ? እውነቴን ነው የምነግራችሁ! ሰይጣን ሲጀመር እውነት ይናገራል?አይናገርም!" እስመ ሀሳዊ ውእቱ አቡኋ ለሀሰት" መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈው ይሄ ነው የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 8 ላይ እሱ የሀሰት አባቷ ነው "ወሶበ ይነብብ ሀሰተ እምዚአሁ ይነብብ" ሀሰትንም ሲናገር ከራሱ አመንጭቶ ይናገራል ብሎ ነው የሚናገረው።
ሰይጣን የእኔ ነው ያለውን ሁሉ… እንግዲህ ሰይጣን ቤተክርስቲያን የእኔ ናት ቢል ልንሰጠው ነው?አንሰጠውም!

አንዳንዶች ደግሞ ባለዛሮችና ጠንቅ ዋዮች ይጠቀሙበታል ይላሉ። እንዴ? በግን እንግዲህ ጠንቋዮች ያርዱታልና እኛ አንበላም ልንል ነው? ኃጥያት ነው ሊባል ነው?ስንዴኮ ከሙስሊም ቤት ቂጣ ሆኖ ይፈተታል ከእኛ ቤት አይበላም ልንል ነው?ሰው እንዳጠቃቀሙ ፍጥረትን ይጠቀምበታል ራሱም ያረክሰዋል። ቡና የረከሰ ፍጥረት ነው የሚል ፈፅሞ የለም።ቡና ለምን ሰተት ብሎ እንደገባ አላቅም። እንኳን መጣ ግን!

አንዳንዶቹ ደግሞ ቆሮንቶስ መልዕክት ላይ ቅዱስ ጳውሎስ የአጋንንትን መጠጥና የእግዚአብሔርን መጠጥ አንድ ላይ መጠጣት አትችሉም ብሏል ይላሉ።የአጋንንትን መጠጥና የእግዚአብሔርን መጠጥ አንድ ላይ አትጠጡ አለ እንጂ ቡና የአጋንንት መጠጥ ነው አላለም።የአጋንንት መጠጥ የተባለው ከጣኦት ቤት የሚሰራ ማንኛው ነገር። ከጣኦት ቤት ከተሰራ፣ ባለዛሮች ስም ከጠሩበት፣ ጠንቋዮች ከደገሙበት የአጋንንት ስም ከተጠራበት ቡና ብቻም ሳይሆን እንጀራም አይበላም ጠላም አይጠጣም ማንኛውም ነገር ከአጋንንት ቤት ከሆነ የረከሰ ነው።

✓በዛ ላይ ደግሞ እንዲህም አይነት ጥያቄ ይነሳል" ቡና ጌታ የተሰቀለ እለት ለምልሞ ነው ሁሉም እፅዋት ሲያረግፉ"ቡና ክርስቶስን ምን በድሎት?ክርስቶስ ቡናን ምን በድሎት ነው ለምልሞ የዋለው? ይሄ ነውር አይደለም? ከፍጥረት ወገን ከሰውና ከሰይጣን በስተቀር ግዕዛኑን ያፋለሰ ለክርስቶስ መገዛቱን ያፋለሰ ማንም ፍጥረት የለም እንጨትም በሉት ድንጋይም በሉት ሁሉም ለክርስቶስ ተገዝቷል። እንደዚህ የሚል መጽሐፍም ፈጽሞ የለም። ቤተክርስቲያን አራት የመጽሐፍትትምህርት ቤቶች አሏት ብሉይ፣ሐዲስ፣ሊቃውንትና መነኮሳት።በአራቱም ጉባኤያት ውስጥ ቡና አይጠጣም የሚልና ክርስቶስ የተሰቀለ ዕለት ለምልሞ ውሏል የሚል መጽሐፍ ጨርሶ አይገኝም።እንግዲህ የቤተክርስቲያኒቱ ትርጓሜ ቤት ከሌለ ማን አመጣው ሊባል ነው?ከየት ታመጡታላችሁ?ቤተክርስቲያኒቱን ዋናው ወስኖ የሚያኖራት ትርጓሜ ቤቷ ነው።የመጽሐፍ ትምህርት ቤት ያላለውን መናገር ፈጽሞ ነውር ነው።አባቶቻችን አልተረጎሙም ቄርሎስ ብሏል?አፈወርቅ ብሏልን?ቅዱስ ያሬድ ብሏልን?አባ ጊወርጊስ ብሏልን?አቡነ ተክለሀይማኖት ብለሏልን?ወይስ ማን ነው ያለው?አግናጢዎስ ብሏል? ሄሬኒዎስ ብሏል?አላሉም! አቡሊጊስ ብሏል?ሳዊሮስ ብሏል? አላለም!ታዲያ እንግዲያ? ነብያት ሐዋርያት ብለዋል? አላሉም! ከጣኦት ቤት ከተሰዋ ስመ አጋንንት ከጠራበት ግን ሁሉም ክልክል ነው።ይሄንን ነው ለይታችሁ ማወቅ የሚገባው ማለት ነው።

ሌላው ሰው ያሳማል ሰው እንጀራም እየበላ ያማል ጠላ እየጠጣም ያማል ስለዚህ ሁሉንም እንደሚገባ ማድረግ ነው።ከዚያ ውጭ ግን የአጋንንትን ስም አቦል ቶና በረካ እያሉ የሚጠሩ አሉ ይሄ ኃጥያት ነው።ሰው እንደሚጠጣው ሻይ እንደሚበላው እንጀራ ከአስፈለገው መጠጣት መብላት ይችላል ።ሦስት ጊዜ ማፍላት አራት ጊዜ ማፍላት እንትን መጎዝጎዝ እንትን ማጤስ ግን ነውር ነው። አሸንክታብ የሆነውን ነገር መጣል እንደምንፈልገው ምግብ ዝም ብሎ መጠቀም ይቻላል ።ነገር ግን ሰው አልጠጣም ቢል ነውር አይሆንበትም ሰው ስጋ አልበላም ቢል ነውር እንደማይሆንበት።

9 - 0

መምህር ኢሳይያስ - memher esayiyas
Posted 2 months ago

ቅዱስ አማኑኤል
ጳውሎስ ሮሜ ለተባለ አገር ላሉ ምእመናን በጻፈላቸው መልእክት ምን አለ መሰላችሁ? ‹‹…እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል ?…››( ሮሜ ፰፥፴፩) እርሱ ከእኛ ጋረ ከሆነ ክፉ ነግር አያገኘንም፤ ይጠብቀናል፤ ይባርከናል፤ የምንማረውን ጥበብ ማስተዋል ይገልጥልናል፤ ታዲያ ይህ ሁሉ እንዲሆንና እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንዲሆን እኛ ታዛዦች፣ ሰው አክባሪዎች፣ በቤት ውስጥ፣ በትምህርት ቤት ታማኞች፣ ለሰው መልካም ነገር የምንሠራ፣ ሰዎችን የምንወድ መሆን አለብን፤ ያን ጊዜ መልካም እና አስተዋይ ቅን ልጆች ስንሆን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ይሆናል፡፡

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እስኪ እያንዳንዳችን የስማችንን ትርጉም እንጠይቅና እንረዳ፤ ወላጆቻችን ስማችንን ሲሰይሙን (ስም ሲያወጡልን) የራሱ የሆነ ምክንያት አለው ፤ ስም መጠሪያ ብቻ ሳይሆን ማስታወሻም ነው፤ ስለዚህ መልካም ምግባር በመሥራት፣ የጥሩ ነገር አርአያ ሆነን ለመገኘት አስተዋይና ብልህ ልጅ መሆን አለብን፤ ስም በመልካም ሲነሳ ሰው ደስ ይለዋል፤ ከደስታም በላይ ከእግዚአብሔር በረከትን ያሰጣል፤ እንደተሰየመልን ስም ዓይነት መልካም፣ ጠባይና ጥሩ ሥነ ምግባር ያለው ልጅ እንሁን፡፡

መልካም የፈተና ጊዜ ይሁንላቸሁ! በርቱ!  ቸር ይግጠመን !

ስብሐት ለእግዚአብሔር

ወለወላዲቱ ድንግል

21 - 1

መምህር ኢሳይያስ - memher esayiyas
Posted 3 months ago

በአረብ አገር የምትኖሩ የኦርቶዶክስ ልጆች አሐቲ ድንግል የተሰኘውን የአባ ገብረ ኪዳንን መፅሐፍ ባላቺሁበት እንልካለን ለ 50 ሰዎች በነፃ ያ ማለት የመላኪያ ወይም የመቀበያ ሳይከፍሉ የመፅሐፉን ዋጋ ብቻ ከፍለው ልክ እንደ ኢትዮጵያ ማለት ነው ባላቺሁበት አገር እንልካለን። ለሌሎች ደግም ለበለጠ መረጃ በቴሌግራም ዋትሳፕና imo ያናግሩን 0925882229
አላማቺን መፅሐፉን ለእናንተ ማድረስ ነው

28 - 0

መምህር ኢሳይያስ - memher esayiyas
Posted 4 months ago

ለኔ የደረሰ ቅዱስ ገብርኤል ለእናንተም ይድረስላቺሁ🌹🌹🌹

82 - 1

መምህር ኢሳይያስ - memher esayiyas
Posted 4 months ago

✏ታላቅ የምሥራች !!!

👉የምሥራቀ ፀሐይ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ግዥ የፊርማ እና የርክክብ መርሃ ግብር ተከናወነ።


🙏"ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን "
2ኛቆሮ 9፥15

👉በቅድስት ሥላሴ ቸርነት፣ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ በጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ተራዳኢነት፤ ለዓመታት ስንመኘው የነበረው የምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ሕንፃ ግዥ፤ የዲሲና አከባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል፣

👉 የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የሜሪላንድ ደብረ ገነት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳደሪ ሊቀ ማእምራን ፕሮፌሰር ቀሲስ ዘበነ ለማ፣ እንዲሁም የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ እና የሜሪላንድ ኆኅተ ምሥራቅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ አርያም ቀሲስ ብርሃኑ ጎበና በክብር እንግድነት እና እማኝነት በተገኙበት፤

👉የምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ባለቤት የኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መሆኗ በጉልህ በታወቀበትና በተገለፀበት ሁኔታ፤ ሁሉም የደብራችን የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ሥራ አስፈፃሚ አባላት ተወያይተውና መርጠው በፊርማቸው አረጋግጠው ደብሩን (ቤተ ክርስቲያኒቱን) ወክለው በግዥ ሰነዶች ላይ እንዲፈርሙ በወከሏቸው ሦስት አባላት በኩል እንዲሁም በተጨማሪ ሦስት እማኞች ማለትም የዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ (ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል)፣ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ (ቀሲስ ዶ/ር ዘበነ ለማ) እና የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ (ቀሲስ ብርሃኑ ጎበና)

👉 በሕጋዊ መንገድ በተዘጋጀው የግዥ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን ሲያኖሩ፤ አፈፃፀሙም ከቤተ ክርስቲያኒቱ የተሰጣቸውን የአገልግሎት ኃላፊነት በትጋትና በትኩረት ባከናወኑ የሕንፃ ኮሚቴ አባላት፣ ማኅበረ ካህናት፣ የሰ/ት/ቤት አገልጋዮች፣ ማኅበረ ምእመናን እና ሕፃናት በታደሙበት የፊርማ እና ርክክብ መርሃ ግብሩ በዝማሬ በእልልታ እና በደስታ ተከናውኗል።

"እንኳን ደስ አላችሁ "

30 - 0

መምህር ኢሳይያስ - memher esayiyas
Posted 4 months ago

መልአክ የሚለው የግእዝ ቃል ሲኾን “ለአከ” ማለት (ላከ) ማለት ነው፤ ስለዚኽ መልአክ ማለት መልእክተኛ ማለት ነው፤ ይኸውም ሰው የጸለየውን ጸሎት ያቀረበውን መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡ የእግዚአብሔርን ምሕረት ወደ ሰው የሚያመላልሱ ረቂቃን ናቸውና የተሰጣቸው ሥያሜ ነው፡፡

❖ ልዑል እግዚአብሔር ሰባቱን ሰማያት ከፈጠረ በኋላ በዚያው በዕለተ እሑድ መላእክትን “እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ” (ካለመኖር ወደ መኖር) ማእምራን (ዐዋቂዎች) ለባውያን (አስተዋዮች) አድርጎ ፈጥሯቸዋል፡፡ ከነዚኽ መላእክት ውስጥ አንደኛውና የመላእክት አለቃ የኾነው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡

❖ ቅዱስ ሚካኤል የሚመራቸው ነገደ ኀይላት የሚባሉ በኢዮር ሰማይ የሚኖሩ መላእክትን ነው፤ ሊቁ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሥነ ፍጥረት መጽሐፉ ላይ፦

 “ወለራብዕ ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ ኀይላት ወሊቆሙ ሚካኤል ወአንበሮሙ በራብዕ ሰማይ” ይላል አራተኛው ዐሥሩን ነገድ ስማቸውን ኀይላት ሲላቸው እነዚኽም ባለሰይፍ ሲኾኑ የእግዚአብሔርን ወዳጆች ሲጠብቁ ጠላቶቹን ይቀጣሉ፤ የእነዚኽ ነገደ መላእክት አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ሲኾን በኢዮር በአራተኛው ከተማ አስፍሯቸዋል እንዲል፡፡

❖ ሳጥናኤል “እኔ ፈጣሪ ነኝ” ብሎ የክሕደት ንግግርን በተናገረ ጊዜ አስቀድሞ ሰራዊቱን በመያዝ ከነገደ ዲያብሎስ ጋር የተዋጋ መልአክ ነውና፤ ዮሐንስም ስለ ቅዱስ ሚካኤል ኀያልነት በራእ ፲፪፥፯-፱ ላይ፡-

 “በሰማይም ሰልፍ ኾነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ፤ ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ አልቻላቸውምም ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም ዓለሙንም ኹሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ ርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከርሱ ጋር ተጣሉ” በማለት ዲያብሎስን የተፋለመ መልአክ መኾኑን ገልጾታል፤ በዚኽም “መልአከ ኀይል” ተብሏል፡፡

❖ የ99ኙ ነገደ መላእክት አለቃ ስለኾነው ስለ ቅዱስ ሚካኤል ክብር፣ ውበት፣ ምልጃ ማሕቶተ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ያሬድ በመጽሐፈ ድጓው እንዲኽ ይላል፡-

 ╬ “ክብረ ሚካኤል ናሁ ተዐውቀ

በትሕትናሁ ዐብየ ወልሕቀ

ዲበ አእላፍ ዘተሰምየ ሊቀ

ዘይትዐፀፍ መብረቀ ይተነብል ጽድቀ”

(የሚካኤል ክብረ እነሆ አኹን ታወቀ፤ በትሕናውም ፈጽሞ ላቀ ከፍ ከፍ አለ፤ በአእላፍ ነገደ መላእክት ላይ አለቃን የተባለ መብረቅን የሚጐናፀፍ ርሱ ጽድቅን ይለምናል) ይላል፡-

 የ99ኙ ነገደ መላእክት አለቃ ከመኾኑ ጋር ይልቁኑ ዮሐንስ በራእዩ በምዕ 8፡2 ላይ “በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፥ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው” ካላቸው፤ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት በመዠመሪያ የሚጠቀሰው ቅዱስ ሚካኤል ነውና ሊቁ፡-

╬  “እስመ እምአፉሁ ይወጽዕ ነጐድጓድ

ሕብረ ክነፊሁ ያንበለብል ነድ

እምሊቃነ መላእክት የዐቢ በዐውድ

ሚካኤል ውእቱ መልአኩ ለወልድ”

(የወልድ አገልጋዩ ሚካኤል ነው፤ በዙሪያው ኹሉ ካሉት ከሊቃነ መላእክት ይበልጣል፤ የክንፉ መልክ ነባልባላዊ እሳትን ያቃጥላል፤ ከአንደበቱ ነጐድጓድ ይወጣልና)

╬ “አዕበዮ ንጉሠ ስብሐት

ለሚካኤል ሊቀ መላእክት

ዘይስእል በእንተ ምሕረት

መልአከ ሥረዊሆሙ ለመላእክት”

(የምስጋና ባለቤት ክርስቶስ ለመላእክት ጭፍሮች አለቃቸው የኾነ ስለ ምሕረት የሚማልድ የመላእክት አለቃ ሚካኤልን ከፍ ከፍ አደረገው) በማለት ይጠቅሰዋል፡፡

❖ የስሙ ትርጓሜንም ስንመለከት ሚካኤል ማለት ቃሉ የዕብራይስጥ ሲኾን ሚ- ማለት “ማን”፤ ካ- “እንደ”፤ ኤል- “አምላክ” ማለት ነውና ሚካኤል ማለት “መኑ ከመ አምላክ” (ማን እንደ አምላክ) ማለት ነው፡፡

❖ የመልክአ ሚካኤል ደራሲም ይኽነን ይዞ፦

╬ “ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ

ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ጸሐፈ”

(የያሬድ ልጅ ሄኖክ እንደጻፈው ከልዑል ስም ጋር ለተባበረ ስም አጠራርኽ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡

ቅዱስ ያሬድም፡-

 ╬ “መልአከ ፍሥሐ ሚካኤል ስሙ

ለመላእክት ውእቱ ሊቆሙ

መልአኮሙ ሥዩሞሙ

የሐውር ቅድሜሆሙ እንዘ ይመርሆሙ”

(ስሙ ሚካኤል የተባለ የደስታ መልአክ ለነገደ መላእክት አለቃቸው ነው፤ የተሾመላቸው አለቃቸው ርሱ እየመራቸው በፊት በፊታቸው ይኼዳል) ይላል

❖ በብሉይ ኪዳን ለአበው ነቢያት እየተገለጠ፤ ለሐዋርያትም በስብከት አገልግሎታቸው እየተራዳ፤ ለሰማዕታት፣ ለቅዱሳን አበው በተጋድሏቸው እየተገለጠላቸው አስደሳች መልኩን ያዩት ነበር።

❖ ይኽነን የቅዱስ ሚካኤልን ውበት ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይገልጠዋል፡-

╬ “መልአከ ፍሥሐ ዘዐጽፉ መብረቅ

ሐመልማለ ወርቅ ሚካኤል ሊቅ”

(መጐናጸፊያው መብረቅ የኾነ የደስታ መልአክ፤ አለቃ ሚካኤል የወርቅ ዐመልማሎ ነው)

❖ የመልክአ ሚካኤል ደራሲም ይኽነን ውበቱን ሲገልጠው፡-

╬ “ሰላም ለአክናፊከ እለ በሰማያት ያንበለብሉ

ከመ ሠርቀ ፀሓይ ሥነ ጸዳሉ”

(የጸዳሉ ውበት እንደ ፀሓይ አወጣጥ የኾነ በሰማያት ለሚያንበለብሉ ክንፎችኽ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡

❖ ቅዱስ ያሬድ ደግሞ፡-

╬ “ውእቱ ሊቆሙ ወመልአኮሙ ሚካኤል ስሙ

ዐይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ

ሐመልማለ ወርቅ”

(ዐይኑ የርግብ (እንደ ርግብ የዋህ፣ ጽሩይ) የኾነ ልብሱ የመብረቅ መጐናጸፊያ የኾነለት የወርቅ ዐመልማሎ ስሙ ሚካኤል የተባለ ርሱ የመላእክት አለቃቸው መሪያቸው ነው) ይላል፡፡

❖ መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብብ ሙሴን ከፈርዖን፣ ኢያሱን ከአማሌቅ፣ ሕዝቅያስን ከሰናክሬም፣ ዳዊትን ከጎልያድ እጅ በተራዳኢነቱ የጠበቀ ሲኾን፤ ስለ ቅዱስ ሚካኤል አማላጅነትና ተራዳኢነት ነቢዩ ዳንኤል፡- “ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ…ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርኻለኊ በዚኽም ነገር ከአለቃችኊ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም… በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብኽ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል” በማለት አማላጅነቱን መስክሮለታል (ዳን ፲፥፲፫፤ ፲፥፳፩፤ ፲፪፥፩)፡፡

❖ የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነትና አማላጅነት ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይገልጠዋል፡-

╬ በ፲ወ፬ቱ ትንብልናከ ዐቢይ ልዕልናከ

በመንክር ትሕትናከ

አስተምህር ለነ ሰአልናከ”

(በዐሥራ አራቱ ልመናኽ ምልጃኽ፤ በታላቅ ልዕልናኽ በሚያስደንቅም ትሕትናኽ ሚካኤል ትለምንልን ዘንድ ማለድንኽ)

╬ “ዘወሀበ ትንቢተ ለኤልዳድ ወሙዳድ

አመ ምጽአቱ ይምሐረነ ወልድ

ሰአል ለነ ሚካኤል መንፈሳዊ ነገድ

ከመ ንክሃል አምስጦ እምሲኦል ሞገድ”

(ለኤልዳድና ለሙዳድ የትንቢትን ጸጋ የሰጠ የሚኾን ወልድ በሚመጣ ጊዜ ይምረን ዘንድ ከረቂቅ ነገድ ወገን የኾንኸው ሚካኤል ከሲኦል እሳታዊ ሞገድ ማምለጥ እንችል ዘንድ ለእኛ ለምንልን) ይላል፡፡

╬ “ከናፍሪሁ ነድ ዘእሳት አልባሲሁ ዘመብረቅ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ውእቱ ይዕቀብክሙ ነግሀ ወሠርከ ሌሊተ ወመዐልተ”

 (ከናፍሮቹ የእሳት ልብሶቹ የመብረቅ የኾነ የመላእክት አለቃ ሚካኤል በተራዳኢነቱ በጠዋትም፤ በሠርክም፤ በቀንም በሌሊትም ይጠብቃችኊ) እንዲል፤ ሙሴን ከፈርዖን፣ ኢያሱን ከአማሌቅ፣ ዳዊትን ከጎልያድ፣ ሕዝቅያስን ከሰናክሬም፤ ዳንኤልን ከአፈ አናብስት፣ ሶስናን ከረበናት፤ ቅድስት አፎምያን ከዲያብሎስ እጅ በምልጃው የታደገው፤ አስቀድሞም ዘንዶው ዲያብሎስን ተፋልሞ የጣለው ይኽ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በቀንም በሌሊትም ተራድቶ ይጠብቀን እላለኊ (ራእ 12፡7፤ ራእ 13፡1-3)፡፡

❖ ቅዱስ ሚካኤልን ጨምሮ እነዚኽ ቅዱሳን መላእክት ሰው የጸለየውን ጸሎት ያቀረበውን መሥዋዕት ቅድመ እግዚአብሔር በማድረስ የእግዚአብሔርን ምሕረት ወደ ሰው በማምጣት ሰውን ከአምላካቸው ጋር በማማለድ ጸንተው ያሉ እንደኾኑ በብዙ ሥፍራ ላይ ተዘርዝሯል፡-

ለምሳሌ ያኽል (ዘፍ 48፥15፤ ዘጸ 23፥20፤ መሳ 6፥11፤ ኢዮ 33፥23፤ መዝ 33፥7፤ 88፥6፤ 90፥11፤ 1ነገ 19፥5፤ 2ነገ 6፥15፤ ዳን 3፥17፤ 4፥13፤ 8፥15-19፤ ዘካ 1፥12፤ ማቴ 18፥10፤ ሉቃ 1፥19፤ 13፥6-9፤ 15፥7፤ ዮሐ 20፥11፤ የሐዋ 12፥6፤ ዕብ 1፥14፤ ራእ 8፥3-4ን ይመልከቱ)፡፡

70 - 1

መምህር ኢሳይያስ - memher esayiyas
Posted 4 months ago

ገብረ መንፈስ ቅዱስ (በእንግሊዘኛ ፡Gabra Manfas Qeddus) በኢትዮጵያውያን ዘንድ አቦ፣ አቡዬ እየተባሉ የሚጠሩት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በትውልድ ግብፃዊ ናቸው። በአጠቃላይ 562 አመት በዚህች ምድር የኖሩ ሲሆን ከዕድሜያቸው ውስጥ 262ቱን አመት በኢትዮጵያ ሲያሳልፉ የዝቋላን ታላቅ ደብር የመሠረቱና ብዙ ታአምር የሠሩ ፃድቅ ቅዱስ ናቸው ።

71 - 3

መምህር ኢሳይያስ - memher esayiyas
Posted 4 months ago

በገና በተመጣጣኝ ዋጋ ይደውሉ ይዘዙን በውጭም በውስጥም ያላቺሁ ደውሉና እዘዙኝ 0925882229

21 - 1

መምህር ኢሳይያስ - memher esayiyas
Posted 4 months ago

ሰበር ዜና
ከሳምንት በፊት ከጉባኤ ላይ በደህንነቶች ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብሎ ተወስዶ ለእስር ተዳርጎ የነበረው ቴዎድሮስ (ቴዲ ዘሩፋኤል) ዛሬ ከእስር ተፈቷል::

30 - 3

መምህር ኢሳይያስ - memher esayiyas
Posted 5 months ago

“ሰማዕት” የሚለው ቃል ዘሩ ‹‹ስምዐ›› ከሚለው የግዕዝ ግስ የሚወጣ ሲሆን ቀጥተኛ ትርጉሙም “ምስክር” ማለት ነው፡፡ “ሰማዕትነት” ማለትም እንዲሁ “ምስክርነት” ማለት ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም ሰማዕት ማለት የተሰዋ፣ ራሱን መስዋዕት ያደረገ ማለት ነው፡፡ የዚህም ምስክርነት ዋና መሰረቱ ጌታችን በወንጌሉ “በሰው ፊት የሚመሰክርልኝን በሰማይ አባቴና በመላእክቱ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ሁሉ ፊት የሚክደኝን በሰማይ አባቴና በመላእክቱ ፊት እክደዋለሁ (ማቴ 10፡32)” ብሎ የተናገረው ታላቅ ቃል ነው፡፡ ከመጀመሪያው ሰማዕት ከአቤል ጀምሮ እስከ ህጻናተ ቤተልሔም፣ እንዲሁም የበራክዩ ልጅ ካህኑ ዘካርያስ፣ መጥመቀ መለኮት ዮሐንስ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ፣ ቅዱስ ጳውሎስ፣ በዘመነ ሰማዕታት የነበሩት እነ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ እነ ቅድስት አርሴማ፣ እነ ቅዱስ ቂርቆስ፣ በእኛም ዘመን በተለያዩ ስፍራዎች ሰማዕትነትን የተቀበሉት ግብጻውያን እና ኢትዮጵያውያን እና የመሳሰሉት ይህንን በመመስከር ለታላቅ ክብር ከበቁ ሰማዕታት መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

63 - 0