Channel Avatar

Debtera Media @UCQi6pyJxgujHwhGfbV4RVuw@youtube.com

18K subscribers - no pronouns :c

Debtera Media is the voice of truth. Be a family by subscrib


Welcoem to posts!!

in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c

Debtera Media
Posted 11 months ago

አቡነ ሉቃስ የእባቡን መርዝ እያስተፉት ነው። [አይበሉም እንጅ] በርገር መብላት ዕጸ በለስ መብላት አይደለም። ዕጸ በለሱንም ዕጸ ሲጥራጢሱንም የማይለቁት ሰውዬ አውግዣለሁ ቢሉ የሚሰማቸው የለም።

መጀመሪያ ሆድህን አውግዝ!


Subscribe👉 bit.ly/3bMfT8D

160 - 5

Debtera Media
Posted 11 months ago

የጃውሳዎች ጃውሳ

ጃውሳው ካሣ
ከቱርክ ይዋጋል እንኳን ከአንካሳ

እንዲሉ ራሳቸው

ጥር ፮ ቀን ከተወለዱ ፪፻፭ (205) ኾናቸው። በ፲፰፻፲፩ (1811) ዓ.ም. ነው ልደታቸው።

Subscribe ‪@DebteraMedia‬

129 - 5

Debtera Media
Posted 11 months ago

"ከሃይማኖቴ ጋር የእኔ ነፍስ ትወጣለች። በሃይማኖት አንደራደርም" አቡነ አብርሃም

ትናንት ከቆሙበት የመስቀል ዐደባባይ ዛሬም ያልወረዱ አባት። ቤተ ክርስቲያን የሕልውና አደጋ ስለደረሰባት ለመጨረሻው ጸዋትወ መከራ እንዘጋጅ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በመግለጫቸው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች

+ + + + +


፩. ቤተ ክርስቲያን የራሷ ነፃነት አላት

፪. ያም ይኽንን አድርጊ ይሄም ይኽንን አድርጊ ስላላት እየተጎች የተባለችውን የምታስተናግድ አትኾንም አይደለችምም።

፫. ማንም ይኽን አድርጊ እያለ ሊጎትታት አይችልም። ነገር ይኽንን በሉ ይኽንን ካላደረጋችሁ የሚባል መያዣ ነገር ቤተ ክርስቲያን አስተናግዳም አታውቅም። ወደፊትም አታስተናግድም። ወደፊትም የመጣውን በጸጋ ከምትቀበል ውጭ። ይኽንን አድርጊ ስልሽ ብቻ ነው የምታደርጊው የሚለው አስተሳሰብ ጨርሶ የቤተ ክርስቲያንን ሕልውና ይነካል።

፬. መንግሥት በዓለ ጥምቀትን ለማክበር ቅድመ ኹኔታ ማስቀመጡን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ በመግለጫቸው ጠቁመዋል። [የአቡነ ቄርሎስን እና የአቡነ ሉቃስን] አቋም በበዓሉ እንድታወግዝ መንግሥት አቋም ይዟል።

፭. መንግሥት አኩራፊ ሊኾን አይገባውም። ይኼንን ካላልሽ እንዲህ አላደርግም ማለት አይገባም።

፮. ሱሪ በአንገት አውጣው የሚባል ነገር ቤተ ክርስቲያን አትሸከምም

፯. መኪና ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ሲገባ የማይፈትሹ ሲወጣ የሚፈትሹ የመንግሥት ጥበቃዎች አሉ። የሚገባ መኪና አይፈተሽም የሚወጣ መኪና ይፈተሻል። ምንድን ነው የተፈለገው? ከቤተ ክርስቲያንስ ምንድን ነው የሚወጣው? መድፍ ነው? መሣሪያ ነው?

እኛ መሪዎቹ የማናውቀው ፈታሽ አቁሞ መፈተሽ ድፍረት ነው። የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕልውና መፈታተን ነው።

፰. መደፋፈሩ በዝቷል። መንግሥት ቤተ ክርስቲያኒቱን ደፍሯታል። አልፎ ይሔዳል። ቤተ ክርስቲያንን መድፈር አደጋ ነው። ለሃይማኖቱ የማይሞት የለም።

አዛዣችን በዝቷል። ላዘዘን ኹሉ አጎንብሰን እንችላለን እንዴ? ሃይማኖታችን ከሚፈቅደው ውጭ። በሉ የተባልነውን ኹሉ ማለት እንችላለን እንዴ? ለእኔ አድርግ የሚለኝ ሃይማኖቴ ብቻ ነው። ማስፈራሪያ አይገዛንም። ዘጠኝ ሞት መጣ ቢሉት አንዱን ግባ በለው።

፱. በየሔድንበት በየቢሮው ደሞ ለኦርቶዶክስ? እየተባልን ነው። ቢያንስ አይኾንም እንኳ [የአባት ነው] አትቁም ያሉት ለማኝ አትቁም ነው። ያንን ያንን ያርሙ።

እዚህ እኛው ቤት አድር ብዬው ቅጥረኛው ስለሚበዛ ነው። የድፍረት ኃጢአት በዝቷል። ድፍረት የቤቱን ሰው ገዝቷል የውጭውንም ሰው ገዝቷል። የማትደፈረውንም ቤተ ክርስቲያን እያስደፈረ ይመጣል። አኹን የቀረው በሉ ውጡ ብሎ የመረካከብ ሥራ ነው ይኽች ቤተ ክርስቲያን የቀራት። ይኽንን ደግሞ ቆሞ የሚያይ የለም።

የጎጠኝነቱ ምንጩ ቤተ ክህነቱ ኾኗል። ከሃይማኖቴ ቋንቋዬ ይበልጣል የሚሉ ሰዎች የተነሡበት ጊዜ ነው። ስወለድ ቋንቋዬን ይዤ ነው የተወለድኹት ሃይማኖት በኋላ ነው የመጣ ነው የሚሉ ካህናት የተፈጠሩበት ወቅት ነው።

፲. ከሃይማኖቴ ጋር የእኔ ነፍስ ትወጣለች። በሃይማኖት አንደራደርም።

አንበርክኬ ልግዛ የሚለው ይቁም

ለመጨረሻው ጸዋትወ መከራ ራሳችንን እናዘጋጅ!


በተጨማሪም ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን በተመለከተ የተናፈሰውን ወሬ በጸና ቃል እስከሞት በሚደርስ ትምምን በመግለጽ በትነውታል።

‪@DebteraMedia‬

123 - 11

Debtera Media
Posted 1 year ago

በእውነት ይህንን የሚመስል አዋጅ ሰምተን እናውቃለን? ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን የምሥራችን ያስከተለ ልደትን ማን ተወለደ? በመላው ዓለም ለሚገኙ የሰው ልጆች ሁሉ “ተወልዶላችኋል” ተብሎ ዜና ልደቱ የተነገረለትስ ማን አለ? ሔዋን በምድር ላይ መውለድን በጀመረች ጊዜ ይህ ዐዋጅ አልነበረም። ሣራም በእርጅናዋ ወራት ፀንሳ በወለደች ጊዜ “ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ የምሥራች እነግራችኋለሁ” የሚል መልአክ አልተላከልንም። ከሔዋን በፊት በምድር ላይ ፀንሳ የምትወልድ ሴት አልነበረችም። ከሣራም በፊት በእርጅናዋ ጊዜ የወለደች ሴት አልተገኘችም። ነገር ግን ይሄ ሁሉ ነገር ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን የምሥራችን ይዞልን አልመጣም። ምክንያቱም የተወለደው ክርስቶስ አይደለምና። ልደታቸው ለመደነቅ ምክንያት የነበረው ልደት ነው፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የእናቱን ማኅፀን ከፍቶ የሚወጣ ልጅ ልደቱ ሊደነቅ ይገባዋል በምድር ላይ መኖር የጀመሩት አዳም እና ሔዋን በዚህ መንገድ አልተገኙምና። በምድር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ዘጠኝ ወራትን ፀንሳ የወለደች ሴትንም ማየት ያስደንቃል አዳም ሔዋንን ከጎኑ ባስገኛት ጊዜ እንዲህ ያለ ሥርዐት አልነበረምና። በእርጅናዋ ወራት በመውለዷ የሣራም ፅንስና የይስሐቅ ልደት እንዲሁ አስደናቂ ልደት ነበረ። እናቱ ሣራ ስለ ይስሐቅ ስትናገር “እግዚአብሔር ሳቅ አድርጎልኛል ይህን የሚሰማ ሁሉ በእኔ ምክንያት ይስቃል” ዘፍ 21፥6 ብላለች። ይሁንም እንጅ የወለደችው ልጅ ለሰሙት ሁሉ ሳቅ የሚሆንላቸው በእሷ ምክንያት ነው እንጅ በተወለደው ልጅ ምክንያት አልነበረም። በዘጠና ዓመቷ ወልዳለችና። ከወለደችም በኋላ “ደግሞም ሣራ ልጆችን እንድታጠባ ለአብርሃም ማን በነገረው? በእርጅናው ልጅን ወልጄለታለሁና” ብላ የምሥራቹን ወደ አብርሃም ልካለች እንጅ ለዓለም ሁሉ የምሥራች ተብሎ አልተነገረም።

ከዚህ ሁሉ የተሻለ የደስታ ዜናን የያዘው የመጥምቁ ዮሐንስ ልደት ነው “በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል” ሉቃ 1፥14 ተብሎለታልና። ጊዜው የክርስቶስ ልደት እየተቃረበ የነበረበት ወቅት ነበርና በመወለዱ ተድላ ደስታን ለብዙዎቹ የሚሰጥ ፅንስ ከሴቶች ማኅፀን መገኘት ጀመረ። ነገር ግን ደስታው ከወገኖቿና ከጎረቤቶቿ ከዘመዶቿም ያለፈ አልነበረም “ጎረቤቶቿም ዘመዶቿም ጌታ ምሕረቱን እንዳገነነላት ሰምተው ከእርሷ ጋር ደስ አላቸው” ተብሏልና ሉቃ 1፥58። ሌሎችም አሉ መልካም እንደሆኑ አይተው ሰዎች የራሩላቸው፣ ባዕዳን የወደዷቸው ነበሩ ዘፀ 2፥2፣6 ነገር ግን ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ የምሥራች ይዘው አልመጡም። ስለዚህ ዐዋጅ ነጋሪ መልአክ መጥቶ “ደስ ይበላችሁ” አላለንም፤ ከእነሱ መካከል እኛን ሊያድን የተወለደ መሢሕ የለምና። እነዚህ ሁሉ የእናትና የአባቶቻቸውን ርስት ወርሰው ይኖራሉ እንጅ እኛን ሊያወርሱን የሚችሉት ርስት የላቸውም። በታላቅ ደስታ እንደሰት ዘንድ ምን ምክንያት አለን? እነዚህ ሁሉ ልጆችን ወልደው ምድርን ቢሞሏትም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጀምሮ የተገፋችውን መንግሥተ ሰማያት ለተገፉት ሐዋርያት ማውረስ የሚቻለው ማንም አልነበረም ማቴ 11፥12።

ዛሬ ግን ለሁሉም የሚሆን ልደትን የተወለደ የክርስቶስን ልደት እንሰማ ዘንድ እግዚአብሔር መላእክቱን ላከልን። ድንግል በድንግልና ፀንሳ እንደምትወልድ ትንቢት የተናገረ ኢሳይያስ ዛሬ በምድር ላይ የለም። እግዚአብሔር በተዘጋ በር ሳይከፍት ገብቶ ሳይከፍት ሲወጣ በራዕይ ያየው ባለ ራዕዩ ሰው ሕዝቅኤልም በአጠገባችን አይደለም። ጌታ የተወለደባትን ስፍራ “አንች ቤተ ልሔም የይሁዳ ነገሥታት ከነገሡባቸው አህጉር ብትበልጪ እንጂ አታንሺም” ብሎ ቦታውን ያሳየን ሚክያስም ቤተ ልሔም ላይ አልታየም። እነዚህ ሁሉ ትንቢት የተናገሩለት መሢሕ እስኪመጣ ድረስ በዚህ ዓለም ሆነው አልጠበቁትም በመቃብር ሞት እየገዛቸው የተነገራቸው ተስፋ ይጠባበቁ ነበር እንጅ አንዳቸውም በምድር ላይ አልነበሩም። ስለዚህም እግዚአብሔር መላእክትን ልኮ ዜና ልደቱን ነገረን።

በዳግመኛ ምጽአቱ ጊዜ በመላእክት አለቃ ድምጽ የሚቀሰቅሰን ነውና ዛሬም የመላእክት አለቃ ገብርኤልን ልኮ ወደ ልደቱ ጠራን 1ተሰ 4፥16። ዛሬ ተወልዶ ያየነው በኋላ ከሰማይ ሲወርድ የምናየው ክርስቶስ ነው። አሁን “እነሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ” ብሎ የነገረን መልአክ በኋላም በነጋሪት ድምጽ ከመቃብራችን የሚቀሰቅሰን መላክ ነው። ዛሬ አዋጅ ነጋሪው መላክ የተላከው የተወለደውን ክርስቶስን ሊያሳየን ነው በኋላም የሚላከው ከሰማይ የሚወርደውን ክርስቶስን ወርደን እንድንቀበል ነው። አሁንም ክርስቶስ በኋላም ክርስቶስ። በኋላ በእልፍ አእላፍ መላእክት ታጅቦ በታላቅ ግርማ ተከቦ የሚመጣውን ክርስቶስን ዛሬ በግርግም ተጥሎ አየነው። ይህ ቀን ለእኛ ከቀናት ሁሉ የሚበልጠው ቀን ነው። ይህንን ቀን እስካሁን ካለፉት ቀናት በየትኛው ቀን ታመሳስሉታላችሁ? ዓለም በተፈጠረባት ቀን ነውን? ወይስ አዳምን በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው በተባለው ቀን ነው? ሕዝቡን ነጻ ያወጣቸው ታላቁ ሰው ሙሴ በተወለደበት ቀን ነውን ወይስ ነገሥታቱ ዳዊት ሰሎሞን በተወለዱበት ቀን ነው? በእውነት ለዚህች ቀን ምሳሌ ሊሆን የሚችል ቀን ከየት እናገኛለን?

ሰማይና ምድር የተፈጠሩበትን ቀን እንዳናደንቅ የሚያልፉበትም ቀን አላቸው ማቴ 24፥35 ቅዱሳን ወርሰውት የሚኖረውና የማያልፈው ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬ ተወልዶልናል። በሰማይና ምድር የልደት ቀን ያልነበርን እኛ የሰማይና የምድር ፈጣሪ ልደት ሲከበር በክብር ተጠራን። ሔሮድስ ለልደቱ ዘፍነው ደስ የሚያሰኙትን እንጅ እኛን ሁላችንን አልጠራንም ክርስቶስ ሲወለድ ግን ሁሉም ተጠርቷል። ልደቱን የምናከብርለት ክርስቶስ እንደ ሔሮድስ ዘፍነን ደስ እንድናሰኘው የሚፈልገን አይምሰላችሁ በመወለዱ ለሁላችን የሚሆን ታላቅ ደስታን የምሥራችን ሊሰጠን ነው እንጅ። በዕለተ ልደታቸው በልተው ጠጥተው ከወገኖቻቸው ጋር ደስ የሚላቸው ብዙ ናቸው ዳን 5፥1 ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ደስታን ስለሚሰጡ ልደታቸውን የምናከብርላቸው ልጆችን የወለዱልን ሴቶች ግን የሉም።

አዳም በተፈጠረበት ቀን በእግዚአብሔር መልክ ተፈጥሯልና ደስ ብሎን ነበር፤ ነገር ግን ከዚያ የሚበልጥ ነገር ዛሬ ተደረገልን፤ እግዚአብሔር እራሱ በአዳም መልክ ተወለደልን። ይህንን ለማየት ወደ ቤተ ልሔም የማይሄድ ማነው? ኑ እስከ ቤተ ልሔም እንሂድ በኢሳይያስ የተጻፈችውን ድንግል እናገኛታለን። ኑ! ሁላችንም እንሂድ ድንግልናዋን ሳትለቅ እናት የሆነችውን ሴት አይተን እንደነቃለን። ኑ! እንሂድ፥ በሰማይ ያለ እናት የተወለደውን በምድር ያለ አባት ተወልዶ እናገኘዋለን። ሰማያዊ አባት ያለውን ክርስቶስን ከምድራዊት እናቱ ተወልዶ እናየው ዘንድ ኑ! እሳት በጨርቅ ሲጠቀለል አይተን እንድናደንቅ ኑ! የልዑል ኃይል የፀለላት፣ መንፈስ ቅዱስ ያደረባት ሴት ዛሬ በመካከላችን ናት ኑ እናክብራት። ማን ያሳየናል ብለን እንዳንቀር የሰማይ ከዋክብት ሳይቀሩ ወደዚህ ስፍራ እየመሩ ይወስዳሉ።

እመቤታችን ጌታን በወለደችበት ቀን በእንግዶች ማረፊያ መብል መጠጥ ቀርቦ ዘፈን ጨዋታ ይደረግ ነበር። ዛሬ መብል መጠጥ ተሰናድቶ ዘፈን ጨዋታ የሚደረግባቸውን ስፍራዎች ሁሉ ቅዱስ ሉቃስ “በእንግዶች ማረፊያ ለማደሪያ ስፍራ አልነበራቸውምና” ሉቃ 2፥7 ብሎ የገለጻቸው ስፍራዎች ናቸው። ለእኛ በእንግዶች ማደሪያ ካሉ ሰዎች ጋራ መዝናናት ምን ያደርግልናል? የዓለም በኵር ክርስቶስ የተወለደው እኮ በእንግዶች ማረፊያ ውስጥ አይደለም። ጌታ የተወለደው ለእኔ ነው የሚል ሁሉ በዓሉን ጌታ በተወለደበት ግርግም ተገኝቶ በዝማሬ ማክበር ይገባዋል። እስኪ ተመልከቱ በዚያ ቀን በዓሉን ካከበሩት መካከል ክርስቶስ ወዳለበት ቦታ ያልሔደ ማነው? መላእክት፣ ነገሥታት፣ ኖሎት፣ እንስሳት ሁሉ ተገኝተዋል። እኛ ግን ልደቱን ለማክበር ጌታ ወዳልተወለደበት ስፍራ ለምን እንሔዳለን? ምንም እንኳን ለማኅሌት የሚሆን መዝሙር ባናጠና እስትንፋስ ካለን በቂ ነው። እስትንፋሳቸውን ያሟሟቁት እንስሳት ሳይቀር በቅዱስ ወንጌል መጻፋቸውን አትርሱ። ወርቅ በሳጥናቸው ካመጡለት ነገሥታት እኩል ባዶ እጃቸውን የመጡ እረኞችን ታሪክ ስናገኘው አይገርማችሁም? እግዚአብሔር የሚፈልገው በተወለደበት ቦታ ልደቱን እንድናከብር ነው እንጅ ሌላ አይደለም። አዕላፍ መላእክት በሚዘምሩበት ቀን የአዕላፋት ዝማሬ ከተማችንን ሊሞላት ይገባል። ዕልፍ አዕላፋት ሆነን ከዕልፍ አዕላፋት መላእክት ጋር የምናገለግልበት ቀን ደረሰ። ኑ የመላእክትን እንጀራ ተመገቡ፤

19 - 0

Debtera Media
Posted 1 year ago

አቤቱ የሚያሰቃዩኝ ምንኛ በዙ?
✍🏽 ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ እንደጻፉት
ብዙዎች በእኔ ላይ ቆሙ፡፡ ብዙዎች ሰውነቴን አምላክሽ አያድንሽም አሏት፡፡
አንተ ግን አቤቱ መጠጊያዬ ነህ፡፡ ክብሬንና ራሴንም ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ነህ (መዝ. 3፡1)
ነቢዩ ዳዊት ክፉ ቀን ቢገጥመው የጸለየው ጸሎት ነው፡፡ መራራ ቀናት ሀገር ያስለቅቃሉ፡፡ ከዙፋን ያወርዳሉ፡፡ ማቅ ያስለብሳሉ፡፡ ለብቻ ያነጋግራሉ፡፡ መራራ ቀናት እንደ ጣፋጮቹ ቀናት ፈጥነው አያልፉም፡፡ ያስቸግራሉ፡፡ ዳዊት መራራ ለቅሶን እያለቀሰ ይህንን መዝሙር የዘመረው ሳኦል ሲያሳድደው ፣ ጎልያድ ሰይፉን መዝዞ ሲመጣበት በነበረ ጊዜ አይደለም፡፡ ዳዊት አቤቱ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ ብሎ መራራ ቃላትን የተናገረው ወደ ዙፋን ከወጣ በኋላ ነው፡፡
ዳዊት አደገ ፤ በሳኦል ፈንታ ተሾመ ፣ ሚስት አገባ ፤ ልጆች ወለደ፡፡ ነገር ግን ከዚህ ሁሉ በኋላ አስጨናቂ ቀን በዳዊት ላይ መጣ፡፡ ልጁ አቤሴሎም በጠላትነት ተነሣበት፡፡ ኤሎፍላውያን ቢሆኑ ይዘምትባቸዋል፡፡ እነ ሳኦል ቢሆኑ ተከታትሎ ያጠፋቸዋል፡፡ የገዛ ልጁ ፣ የአብራኩ ክፋይ ሕዝቡን አሳምጾ አባቱን ሀገር አስጥሎ አሳደደው፡፡
የእኛም ሕዝብ ዛሬ ላይ እንደ ዳዊት ያለ መከራ ነው የገጠመው፡፡ የሚያሰቃዩት በዙ፡፡ ብዙዎች በራሱ ላይ ቆሙ፡፡ አምላክሽ አያድንሽም እያሉ የገነባውን መቅደስ አፈረሱ፡፡ የሚያሳድዱት ኤሎፍላውያን ቢሆኑ በዘመተ ፣ ፣ እነ ጎልያድም ቢሆኑ ወንጭፉን ይዞ በተጋደለ ፣ እነ ሳኦልም ቢሆኑ ቁርጡን አውቆ ጫካ ገብቶ በታገለ ነበር፡፡ ግን እነ አቤሴሎም ናቸው፡፡ ከአብራኩ የተከፈሉ ፤ ከማዕዱ እየበሉ ያደጉ ፣ አብረውት ሀገር ፣ ቤት የተጋሩ፡፡
እነዚህን ምን ማድረግ ይሻላል? ዳዊት ያልተዋጋው ‘አቤሴሎም ልጅ ነው እውቀት ቢጎድለው ነው’ ብሎ ነው እንጂ ስለማይችል አልነበረም፡፡ ዳዊት አርበኛ ነው፡፡ ነብር በጡጫ ፣ አንበሳ በእርግጫ መስበር የሚችል ፤ የጦር መላ ያለው ጀግና ነው፡፡ ሳይዋጋ ዝም ያለው መልስ ከእግዚአብሔር ነው ብሎ አስቦ ነው፡፡ የሸሸ ሁሉ የተሸነፈ አይደለም፡፡ ዝም ያለ ሁሉ ኃይል በውስጡ የሌለው አይደለም፡፡
በመጨረሻ አሸናፊው ዳዊት ነው፡፡ አቤሴሎሞች የሸሸላቸው ሁሉ የተሸነፈ ፣ የማይመለስ ፣ የማይችል ፣ ከዚህ በኋላ አከርካሪው የተሰበረ ስለሚመስላቸው ሚስቱን ፣ ርስቱን ፣ ቤቱን ሀብቱን ሁሉ ይወርሳሉ፡፡ ዳዊት የተመለሰ ቀን ግን ሬሳቸውም አይመለስም፡፡ አቤሴሎም ዳዊትን ባሳደደው ቀን ያደረገው ይህንኑ ነው፡፡ የዳዊትን የአባቱን አልጋ አረከሰ፡፡ ሚስቱን ዙፋኑን ወረሰ፡፡ ዳዊት ሲመለስ ግን አልተገኘም፡፡ ነፍሱ በምድረ በዳ እንደወደቀች ቀረች፡፡ መጨረሻው አያምርም፡፡ እነ አቤሴሎምን ሥልጣን ሲይዙ አለማያውቁበት ግፉን አታብዙ በሏቸው፡፡
ዳዊትም ‘ተነሥ አቤቱ አምላኬ አድነኝ ፤ የጠላቶቼን መንጋጋ መትተሃልና የክፉዎችንም ጥርስ ሰብረሃልና’ እያለ ይመለሳል፡፡ መዝ. 3፡7
ማስታወሻ :- ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ የአራቱ ጉባኤያት መምህርና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ ሲሆን የመጻሕፍት ደራሲም ናቸው:: ሊቅ ሊቃውንት የጃንደረባው ሚዲያ ዐምደኛ ሲሆኑ ጽሑፎቻቸው ዘወትር ሰኞ የሚነበቡ ይሆናል::
janderebaw.org/አቤቱ-የሚያሰቃዩኝ-ምንኛ-በዙ/

14 - 1

Debtera Media
Posted 1 year ago

#ብፁእ_አባታችን_አቡኑ_አብርሀም

በሀይማኖታቸው የታሰሩትን ለሀይማኖታችሁ ቁሙ ቤተክርስቲያንን ጠብቁ ያልነው እኛ አዛዦቹ እንጅ ልጆቻችን አይደሉም‼️

ስለዚህ መታሰር ያለብን እኛ አዛዦቹ እንጅ ልጆቻችን አይደሉም ስለዚህ እነሱን ልቀቁና እኛን እሰሩን‼️🙏

በረከትዎ ይደርብን 🙏

279 - 7

Debtera Media
Posted 1 year ago

አንድም ምዕመን ወደ ቤተክርስቲያኒቱ ዝር አላለም !


በቀድሞ ስማቸው አባ ኃይለ ማርያም ጌታቸው ይባሉ የነበሩ፣ በሕገወጥ መንገድ ከተሾሙት አንዱ የሆኑና "አቡነ አቤል የምእራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ" በሚል የተሾሙ ናቸው።

በሀገረ ስብከቱ ዋና ከተማ አሰበ ተፈሪ [ ጭሮ ] በምትገኘው ደብረ ጽዮን ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን መንበረ ጵጵስናን በኃይል በመስበር ፣ ምዕመናኑን በጥይት ፣ በቆመጥና በአስለቃሽ ጭስ ጭምር ከቤተክርስቲያኗ በማባረር የከተማው ልዩ ኃይል አዲሱን ተሿሚ ማስገባታቸው ይታወቃል።

አዲሱ ተሿሚ ላለፉት ሦስት ቀናት ብቻቸውን ከቆዩ በኋላ ዛሬ ጧት ምእመኑ ሙሉ በሙሉ ከቤተክርስቲያን መቅረቱን ሲያዩ "ነገሩ እንዲህ የሚሆን ፈጽሞ አልመሰለኝም። በእኔ ምክንያት ቤተክርስቲያኔ በመዘጋቷ አዝኛለሁ" ብለው ማልቀሳቸውን እና ብቻቸውን ጠፍተው ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውን አጠገባቸው የነበሩ ሰዎች ተናግረዋል። በቤተክርስቲያን ላይ በተፈጸመው በደልና በኦርቶዶክሳውያን ላይ በተደረገው ግፍ ያዘነው ምዕመን አንድም ሰው ወደ ቤተክርስቲያኒቱ ዝር ሳይል ቀርቷል፡፡

የት እንዳረፉ የምታውቁ ኦርቶዶክሳውያን የጨለማው ቡድን ሳያፍናቸው ለንሰሐ እንዲበቁ ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ ይደርሱ ዘንድ እገዛ እንዲደረግላቸው ጥሪዎች እየተሰሙ ይገኛል።

† † †
በቴሌግራም t.me/DebteraMedia

69 - 0

Debtera Media
Posted 1 year ago

ውድ የደብተራ ሚዲያ ቤተሰቦች ይሄ ዜና መዋዕል ዩቲዩብ ቻናል ቤተክርስቲያን ነክ ነገሮችን የሚሰራ ሚዲያ ሲሆን ሞኒታይዝ ለመሆን 19 ሰው ብቻ፣ስለቀረው የኛ የሆኑ ልጆችን ሰብስክራይብ በማድረግ እናበረታታ 19 ልጆች ብቻ ነው ሚፈልገው። ሊንኩን በመንካት Subscribe በማድረግ ተባበሩት👇

youtube.com/@-zenamewael

21 - 1

Debtera Media
Posted 1 year ago

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃጥያቷ ሀገሯን መውደዷ ነው!

ብጹዕ አቡነ አብርሃም

273 - 1

Debtera Media
Posted 1 year ago

[ ጾመ ነነዌን በጥቁር ልብስ ብቻ ! ]

- ሰኞ
- ማክሰኞ
- ረቡዕ

ሦስቱን ቀናት በመላው ኢትዮጵያና በዓለም ሁሉ ዙሪያ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን በጥቁር ልብስ ብቻ ጾመ ነነዌን ይጾሙ ዘንድ ቅድስት ቤተክርስቲያን አዋጅ አውጃለች !

† † †

144 - 0