Channel Avatar

WolloTube /ወሎ ቲዩብ @UCJHUq6eFR0aCSn0ZxbVtkcw@youtube.com

37K subscribers - no pronouns :c

Well Came to My Channel Wollo Tube/ወሎ ቲዩብ የኢትዪጵያን ወግ ባህል በ


Welcoem to posts!!

in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c

WolloTube /ወሎ ቲዩብ
Posted 1 week ago

የሀይቅ ሆስፒታል ጉድ!!!!!!
ሀይቅ ሆስፒታል ከአዲስ አበባ በ 430 k.m ከደሴ 30 k.m በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በሀይቅ ከተማ የሚገኝ ሆስፒታል ነው።
ይህ ሆስፒታል ስራ ከጀመረ ጀምሮ በርካታ የሀይቅ እና ተሁለደሬ እንዲሁም አጎራባች #ወረባቦ #አምባሰል #ወረዳን ጨምሮ አገልግሎት እየሰጠ ያለ ተቋም ነው ይህ ተቋም ብር ያለው በገንዘቡ ብር የለለው በጤና መድን ነፃ አግልግሎት ይሰጣል በተጨማሪም ተቋም ላይ የሚመደቡ ባለሙያወች ሆን ተብሎ ብቃት ያላቸው ከሌላ ቦታ በልምድ የሚመጡ ከመሆናቸውም በላይ ለታካሚ ያላቸው እንክብካቤ ይለያል :ፅዳትን በተመለከተ ቆሻሻን ፈልጎ ለማግኘት ማይክሮስኮፕ መጠቀም ግድ ይላል አይደለም ሽታ በአካባቢው መጥፎ ጠረን እንኳን የለም:ውሀ 24 ሰዓት አገልግሎት መብራት አውቶማቲክ ጀኔሬተር ተጠቃሚ ናቸው ከቀላል እስከ ከባድ ቀዶ ጥገና አገልግሎት ሲሰጡ የእናቶች ማዋለድ አገልግሎት በተለይም በኦፕሬሽን ማዋለድ በአማራ ክልል የትኛውም ተቋም ብቃት ያለው ኦፕሬሽን ሰራተኛ አዋላጅ ያለው ተቋም ሀይቅ ሆስፒታል ብቻ ነው !!!ይበል የሚያሰኝ እና ማበረታቻ ሽልማት ቢሰጣቸው ባይ ነኝ ።ቢስተካከሉ ብየ የማምነው በቂ የመድሀኒት አቅርቦት ቢገባላቸው ከዋናው መንገድ እስከ ሆስፒታል ድረስ አስፓልት ቢሆን መንገዱ ታታሪ የሆኑ የሆስፒታሉ ሰረተኞችን እና ታመሚወችን እየፈተነ ይገኛል።
ከመግቢያየ ላይ ጉድ ያልኩት የእንግሊዝ ኛውን Good ለመጠቀም አስቤ ነው HAIK HOSPITAL GOOD HOSPITAL ነው!!! ጥር 14 ደቡብ ወሎ ሀይቅ ሸር በማድረግ ሆስፒታሉ ትልቅ ደረጃ እንዲደርስ እናድርገው !!!

35 - 8

WolloTube /ወሎ ቲዩብ
Posted 4 weeks ago

በሬክተር ስኬል 5.80 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ዛሬ ለሊት በአፋር ክልል ተከስቷል።

በኢትዮጵያ በሬክተር ስኬል 5.80 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ፤ ከለሊቱ 9:52 ሰዓት መድረሱን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤት አስታውቋል። ሰሞኑን ሲከሰቱ ከነበሩት የመሬት መንቀጥቀጦች ዘለግ ላሉ ሰከንዶች የቆየው ርዕደ መሬት፤ ንዝረቱ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ተሰምቷል።

የለሊቱ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው በአፋር ክልል ከአቦምሳ ከተማ 56 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ከአዳማ ከተማ 137 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ መሆኑን ታውቋል።

5 - 1

WolloTube /ወሎ ቲዩብ
Posted 1 month ago

አማርኛን የሚያስተምሩ የአውሮፓ ዩኒቨርሲቲዎች
የአውሮፓ ዩኒቨርሲቲዎች አማርኛ ቋንቋን ማስተማር ከጀመሩ አንድ ክፍለ ዘመን ተቆጥሯል፡፡
የጀርመኑ ሐምቡርግ ዩኒቨርሲቲ በአማርኛ ቋንቋ ዙሪያ ባዘጋጀው ጉባኤ በሴሜቲክ ቋንቋዎች ምድብ ስር ካሉ ቋንቋዎች ውስጥ አማርኛ በተናጋሪ ብዛት ከአረብኛ በመቀጠል ሁለተኛው መሆኑን ገልጿል።

5 - 0

WolloTube /ወሎ ቲዩብ
Posted 1 month ago

"የሞት ስአት" የምንሞትበትን ቀን የሚተነብየው አወዛጋቢ መተግበሪያ
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ አስተውሎት) እየተስፋፋ መሄድ ግን የሰው ልጆችን የመሞቻ ቀን የሚተነብዩ መተግበሪያዎች በብዛት እንዲቀርቡ እያደረገ ነው።
በሀምሌ ወር የተዋወቀውና ለመሞት ምን ያህል ቀን፣ ስአት እና ደቂቃ እንደቀረን ይተነብያል የተባለው "ዴዝ ክሎክ" ወይም የሞት ስአት የሚሰጠው ትንበያ የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቧል።
መተግበሪያው ሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚጠቀም ነውና እንደ ህክምና ባለሙያ አስተዛዝኖ ሊነግር ወይም እድሜን ሊጨምር አይችልም የሚሉ ባለሙያዎችም ዝግጁ ያልሆኑ ሰዎች ባይጠቀሙት ይመክራሉ።
ስለ መተግበራያው ዝርዝር በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ bit.ly/3ZBC8aW

5 - 0

WolloTube /ወሎ ቲዩብ
Posted 2 months ago

ከ100 ሺህ በላይ የዩክሬን ወታደሮች ከጦር ግምባር መጥፋታቸው ተገለጸ
አንድ ሺህ ቀን ያለፈው የዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣን ከመያዛቸው በፊት በርካታ አዳዲስ ነገሮችን እያስተናገደ ይገኛል፡፡
ዩክሬን በየጊዜው የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ እያደረገች ሲሆን 100 ሺህ ያህል ወታደሮቿ ከጦር ግምባር ጠፍተዋል ተብሏል፡፡
ከጦር ግምባር የጠፉ ወታደሮችን፣ ወታደራዊ አመራሮችን እና ተንታኞችን ዋቢ በማድረግ በወጣው መረጃ ወታደሮች የመዋጋት ፍላጎታቸው በየጊዜው እየቀነሰ መጥቷል ተብሏል።

3 - 0

WolloTube /ወሎ ቲዩብ
Posted 2 months ago

ከባድ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በ500 ሄክታር ላይ የተዘራ የደረሰ ሰብልን አወደመ

#Ethiopia | በአማራ ክልል ደባርቅ ከተማ አሥተዳደር የገጠር ቀበሌዎች በጣለው ከባድ በረዶ ምክንያት ሰብላቸው ሙሉ በሙሉ በመውደሙ ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን አርሶ አደሮች ተናግረዋል።

ኅዳር 14/2017 ዓ.ም ከቀኑ ስምንት ሰዓት ጀምሮ ለ30 ደቂቃ የጣለው ከባድ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በሶስት ቀበሌዎች ከ500 ሄክታር መሬት በላይ የደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት አድርሷል።

ጉዳቱ በተለያዩ የሰብል አይነቶች ላይ የደረሰ ሲሆን ስንዴ፣ ገብስ፣ ጤፍና ጥራጥሬ ሰብሎች ይገኙበታል።

አርሶ አደሮቹም በአካባቢው ባሕል መሰረት ሰብላቸውን በደቦ ለመሰብሰብ ነገ ዛሬ በሚሉበት ወቅት ድንገት የጣለው በረዶ ሰብላቸውን ሙሉ በሙሉ እንዳወደመባቸው ተናግረዋል።

አቶ ራራ ደሴ የተባሉ የጉዳቱ ሰለባ የሆኑ አርሶ አደር በደረሰው ጉዳት በማዘንና በመደናገጥ በርካታ አርሶ አደሮች ለከፋ የጤና ቀውስ መዳረጋቸውን አንስተዋል።

"ጉዳቱ ያልተጠበቀ ነው፤ እንኳን እኛ እንስሳቱ ራሱ የሚበሉት ድርቆሽ ሳር አልተረፈም" ሲሉ አርሶ አደሩ ማሬ ታረቀኝ ለአሚኮ ተናግረዋል።

የሰሜን ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ባለሙያው ጥላሁን ዓለም ለአሚኮ እንደገለጹት ከ600 በላይ አርሶ አደሮች ጉዳት ደርሶባቸዋል። በፍጥነት መልሶ የማቋቋም ሥራ መሠራት እንዳለበትም ጠቁመዋል።

የደረሰው ጉዳት ከባድ በመኾኑ አርሶ አደሮችን መልሶ የማቋቋም ሥራ በመሥራት በበጋ መስኖ ሰብል ልማት ምርቱን እንዲያካክሱ ለማድረግ ጥረት እንደሚደረግ የደባርቅ ከተማ አሥተዳደር ግብርና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ በዕውቀት አየነው ተናግረዋል።

በጎ ፈቃደኛ ግለሰቦችም ሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች አርሶ አደሮችን መልሶ በማቋቋም ሥራው ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።

Via አሚኮ

19 - 2