in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c
የማቴዎስ ወንጌል 28:20
እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።
የዮሐንስ ወንጌል 3:5
ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል። እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:8
ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤
እንኳን አደረሳቹ 🙏
57 - 2
የሳቱን ነበልባል ውሀ እያደረገ
💒 የእግዚአብሔር መልአክ ነብሳቱን ታደገ
አንዳች ሳይነኩ ከእሳቱ ወጡ
የእግዚአብሔርን ክብር ለዓለም ገለጡ
እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ
ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! 🤍🙏🏻❤
106 - 5
የያሬድ ውብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ስጦታዬ ነሽ
በምን አንደበቴ እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ
ምድርና ሰማዩ ታምርሽን ይንገሩ
ፍጥረታት በሙሉ ስለ አንቺ ይመስክሩ
ተነግሮ የማያልቅ ድንቅ ነው ሥራሽ
ድንግል ሆይ እናቴ አምሳያም የለሽ
ማርያም ድንግል እረዳቴ
የምትደርሽልኝ ነይ ስልሽ በጭንቀቴ
ታምርሽን በዓይኔ አይቻለሁ
ጽዮን ሆይ ስልሽ ድንግል ሆይ እጠግባለሁ
የእግዚአብሔር ጥበቡ ባንቺ ተገለጠ
የአዳም ዘር በሙሉ ከሞት አመለጠ
የመዳን ምክንያት ማርያም አንቺነሽ
ለፍጥረቱ ሁሉ መሰላል የሆንሽ
ነገን ባላውቅ እኔን ቢያስፈራኝ
አንቺ ካለሽኝ በፍጹም አልወድቅም
በፊትሽ እንድቆም በምስጋና
ማርያም ልበልሽ በትህተና
ትውልዱ በሙሉ ለምስጋና ይቁም
በአንቺ ስለሆነ የቀረለት መርገም
አዳም ከነልጁ በሰማይ በምድር
ማርያም ማርያም ይበል ታምርሽን ይናገር
ጨለማው ከፊቴ ተገፈፈ
ማርያም በምልጃሽ ልቤ አረፈ
ከጎኔ ነሽ ስልሽ እጽናናለሁ
እሳት ገደሉን ሁሉን አልፈዋለሁ
አሜን አሜን አሜን እንኳን ለናታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ግሸን ደብረከርቤ ዳግማዊ ጎልጎታ ግማደ መስቀሉ መገኛ ታላቅ ዓመታዊ ክብር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!
235 - 17
Couple based in France rooted in Ethiopia ;) In love with good food and nature and handmade crafts.
Enjoy the journey with us.