in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c
ሰበር ዜና ፦ ቅዱስ ሲኖዶስ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ ሕገወጥ ሢመት የፈጸሙ ጳጳሳትን ከቤተክርስቲያን አንድነት አውግዞ ለየ !
ቀጥታ ስርጭቱን በዚህ ሊንክ ይመልከቱ youtube.com/live/FrwdH9_gsA4?feature=share
ሐምሌ 26 ቀን 2016 ዓ.ም (ፈ.ገ.ሚ/ባሕር ዳር)
ቅዱስ ሲኖዶስ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ ክህደት የፈጸሙ ጳጳሳት ተግባራቸው ምንፍቅና በመሆኑ በሕይወታቸውም ሆነ በሞታቸው የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት እንዳያገኙ በመወሰን ከቤተ ክርስቲያን አንድነት አውግዞ ለየ።
የተወገዙት የቀድሞ ጳጳሳት
"አባ" ኢሳይያስ
"አባ" መቃርዮስ
"አባ" መርሐክርስቶስ
"አባ" ጴጥሮስ ሲሆኑ ተሹመናል የሚሉ መነኮሳትን አውግዞ መለየቱን በአሁኑ ሰዓት እየሰጠ ከሚገኘው መግለጫ ለመረዳት ተችሏል።
52 - 0
የተወደዳችሁ የፈለገ ገነት ሚዲያ ተመልካቾች ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ በዛሬው ዕለት ወደ እናንተ ሥርዓተ ቅዳሴ በቀጥታ ስርጭት እያስተላለፍን ነበር። ነገር ግን ባጋጠመን ከፍተኛ የኔትዎርክና የመብራት መቆራረጥ ምክንያት ሥርዓተ ቅዳሴውን መቀጠል ባለመቻላችን ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡
145 - 5
ለመንግሥት ቀነ ገደብ ተሰጥቷል
ከአዲስ አበባ ሐገረ ስብከት የተሰጠ መግለጫ መግለጫውን በዚህ ሊንክ ይመልከቱ፡፡
youtube.com/live/ioJ7jhSdXwM
257 - 0
የቅዱስነታቸውን ለ፲ኛ ዓመት በዓለ ሢመትዎ በቀጥታ ስርጭት በዚህ ይከታተሉ
https://www.youtube.com/watch?v=tnoBv...
የቅዱስነትዎ ቡራኬ አይለየን !
887 - 4
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የካቲት 16 በዚህች ዕለት አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ከተወደደ ልጇ የማይታበል የምሕረት ቃል ኪዳንን ተቀበለች።
ለእግዚአብሔር ምሥጋና ይሁን፤
እኛንም በእመቤታችን ቃልኪዳን ይማረን፤
በረከቷም ከእኛ ጋር ትሁን፤
ለዘለዓለሙ አሜን!
ዳግመኛም በዚህች ዕለት የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ እናት የቅድስት ኤልሳቤጥ እና የቅዱስ ላሊበላ ታላቅ ወንድም ቅዱስ ገብረ ማርያም/ሐርቤ/ የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው።
ለእግዚአብሔር ምሥጋና ይሁን፤
እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን፤
በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትሁን፤
ለዘለዓለሙ አሜን!
እንኳን አደረሳችሁ!
821 - 19
"ከባንክ አገልግሎት ጋር በተያያዘ በርካታ አሉባልታ ይነሳል፤ቤተክርስቲያን የምትሰራው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ነው።ከዓባይ ባንክ ጋር ሥራ የጀመርነው በህጋዊ አሰራር በጨረታ በተደረገ ሂደት አሸናፊ ሆኖ በመገኘቱ ነው።ከዓባይ ባንክ ይልቅ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በእሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ያለን ገንዘብ ይበልጣል።ዓባይ ባንክ ያለን ገንዘብ ተንቀሳቃሽና ለሰራተኛው የብድር አገልግሎት በማቅረብ ለሰራተኛው የመኪና፣የቤትና የልዩልዩ ግዤዎችን ለመፈጸም የሚያስችል አገልግሎት የሚሰጥበት የባንክ አገልግሎት ነው።
በሌላ በኩል ቤተክርስቲያናችን በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ የማይንቀሳቀስ ገንዘብ አስቀምጣለች። በጣም መጠነኛ ገንዘብ በአዋሽ፣ በሕብረትና በአቢሲኒያ ባንኮች አስቀምጣለች፤ ከዚህ ውጪ በሌላ ባንክ ወይም በአማራ ባንክ የተቀመጠ ምንም አይነት የማዕከላዊ የቤተክርስቲያን አስተዳደር ገንዘብ የለም። የተቀመጠ ገንዘብ አለ ከተባለም በማስረጃ ማቅረብ ይቻላል አሁንም ቢሆን በርካታ ሥራዎችን የምንሰራው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ነው።።"
1.5K - 32
Well Come To Felege Genet Media YouTube Channel
እንኳን ወደ ባህር ዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ቤት የYoutube ቻናል በደህና መጡ ። በዚህ የኢንተርኔት አውደ ምህረት ላይ የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስረዓት የጠበቁ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች |ብሒለ አበው |የዝማሬ አገልግሎቶች | ልዮ ልዮ መንፈሳዊ ዝግጅቶች እንዲሁም የቅዱሳን ክብረ በዓላት በቀጥታ ስርጭት የሚቀርብበት መድረክ ነው።
ውድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ይህን YOUTUBE CHANNEL SUSBSCRIBE በማድረግ የደውል ምልክቱን ተጭናችሁ ALL የሚለውን በመንካት ቤተሰቦቻችን ይሁኑ።
የባህር ዳረ ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ቤት ሚዲያ ክፍል