in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c
#የክርስቶስ_ወዳጆች_በዚህ_ዝማሬ_ተባረኩበት__ለሌሎች ደሞ ወንጌል ስበኩበት
ብሩካን ናችሁ
ለእኔ ህይወት ክርስቶስ ነው
Lene Hiwot/ለእኔ ህይወት/Pastor Biniyam Wale/ ፓስተር ቢኒያም ዋለ
https://youtu.be/HY1cb1gNsGU
17 - 0
በእግዚአብሔር የታመነ ቤተሰብ ይስጣቹ::
1ኛ ሳሙኤል 1
28፤ እኔም ደግሞ ለእግዚአብሔር ሰጥቼዋለሁ፤ ዕድሜውን ሁሉ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ይሆናል።
ኤልዩድ ቢኒያም ዋለ በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን ቶሮንቶ በእሁድ አምልኮ ፕሮግራም ላይ ለጌታ ተሰቷል::የሰጠንን ለሰጪው መልሰን ሰተናል እግዚአብሔር ታማኝ ነው::
Thank you Kali photography
120 - 1
ምን እሆን ብዬ አልሳቀቅም
አብረኸኝ ነህ መቼም አልወድቅም
ብርቱ ነው እጅህ መቼ ይለቃል
ለምስጋና ና ለድል ያበቃል
ማመስገኛዬ ነው ህልውናህ Binyam Wale(Pastor)&Yisakor Negussu ft Dr Beza New Gospel Song(Mezmur)
27 - 1
#ማመስገኛዬ
ስላም ለእናንተ ይሁን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች በእግዚአብሔር ምህረት በዚሁ ሳምንት #ማመስገኛዬ የተሰኘ ዝማሬ ከወንማችን ከዘማሪ ይሳኮር ንጉሱ ጋር የሰራነውን ወደ እናንተ ይዘን እንመጣለን ለእግዚአብሔር ክብር ለቅዱሳን ጥቅም እንዶን በጸሎታችሁ አስቡን::
ወደ ኤፌሶን 1
13፤ እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤
14፤ እርሱም የርስታችን መያዣ ነው፥ ለእግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እስኪዋጅ ድረስ፥ ይህም ለክብሩ ምስጋና ይሆናል።
youtube.com/@pastorbinyamwaleministry5292?si=zhOig…
98 - 1
አትታገሏቸው
በህይወታችሁ ውስጥ የተለያዩ ሰዎች አሉ::ስለ እናንተ መልካም ሚያስቡ:ሚጸልዩላችሁ:ስኬታችሁን ሚናፍቁ ደታችሁ ሚያስደስታቸው:ሀዘናችሁን ማየት የማይፈልጉ:ስታዝኑም አብረዋችሁ ሚያዝኑ: እግዚአብሔር የሰጣችሁ ብዙ ወዳጆች አሉ ስለ እነሱ እግዚአብሔር ይባረክ;ተባርከው ይቅሩ:ዘራቸው ይለምልም::
ደግሞ በተቃራኒ አጠገባችሁ ሆነው ስትደሰቱ የማይወዱ:ሲሳካላችሁ ስኬታችሁን ሚያጣጥሉ:ድካማችሁ ለማየት የሚናፍቁ;ለእነሱ ስታደርጉ ምስጋና ቢሶች;በትንሹ በትልቁ ሚያሳንሱአችሁ;በአፋቸው ሚሸነግላችሁ;አጠገባችሁ ሆነው ሩቅ የሆኑባችሁ........
እነሱን አትታገሏቸው::ሁሌ እናንተ መልካም አድርጉላቸው::ልባችሁ ከእነሱ አንዳች ነገር አይጠብቅ::እናንተ ግን መልካም ከማድረግ አትቆጠቡ::የክርስቶስ ልብ ይህን ያደርጋልና
55 - 0