Channel Avatar

Ewunet Media @UCjiq4hREIdyVsnPPKfSOkcg@youtube.com

206 subscribers - no pronouns :c

የተመረጡ መረጃዎችንና መዝናኛዎችን የምናቀርብበት የናንተው ቻናል ነው። Subscribe በማድረ


Welcoem to posts!!

in the future - u will be able to do some more stuff here,,,!! like pat catgirl- i mean um yeah... for now u can only see others's posts :c

Ewunet Media
Posted 1 week ago

⭕️የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቻይና ምድር የመጀመሪያዋን ደብር ሰየመች

ቤተ ክርስቲያኗ በቻይና ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ በከፈተችው ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቅዳሴ አከናውናለች

ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ በቻይና የመጀመሪያውን አንድ ኢትዮጵያዊ ዲያቆን ሾመዋል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቻይና የመጀመሪያዋን ደብር መሰየሟ ተገለጸ።

በቻይና በቻይና ምድር የተከፈተው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን “ደብረ ምሕረት መድኃኔዓለም” የሚል ስያሜ እንደተሰጠውም የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት መረጃ ያመለክታል።

ሐዋርያዊ አገልግሎት ቻይና የገቡት ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ አዲስ የተከፈተችውን ቤት ክርስቲያን ከሰየሙ በኋላ ሥርዓተ ቅዳሴ በመፈጸም ምዕምናንን ማቁረባቸውም ተነግሯል።
በተጨማሪም ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ በቻይና የመጀመሪያውን አንድ ኢትዮጵያዊ ዲያቆን መሾማቸውም ነው የተገለጸው።

በዕለቱም ከቻይና የተለያዩ ክፍላተ ግዛት የተሰባሰቡ ምዕመናን፣ ቻይናውያን እና ትውልደ ቻይናውያን በሥርዓተ ቅዳሴው ላይ መሳተፋቸውም ተነግሯል።

ከሥርዓተ ቅዳሴው በኋላ በቻይና የሚገኙት በፅዕ አቡን ያዕቆብ ለቀጣይ አገልግሎት ወደ ሀገሪቱ መዲና ቤይጂንግ ከተማ ማቅናታቸውም ነው የተገለጸው።

ሰላም ለሀገራችን @EwunetMediaOfficial

2 - 0

Ewunet Media
Posted 1 week ago

⭕️ሰምተዋል? በአዲስ አበባ ከታህሳስ ጀምሮ የባንክ አካውንት ለመክፈት የ'ፋይዳ' መታወቂያ ማቅረብ ግዴታ ሊሆን ነው
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከቀጣዩ ወር ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ደንበኞች የባንክ አካውንት ለመክፈት “ፋይዳ” የተሰኘውን የዲጂታል መታወቂያ በግዴታነት እንዲያቀርቡ አዘዘ።

ከሁለት ዓመት በኋላ ደግሞ በመላ አገሪቱ የሚገኙ ደንበኞች የትኛውንም የባንክ አገልግሎት ለማግኘት የፋይዳ መታወቂያ እንዲይዙ መገደድ እንደሚጀምሩ ባንኩ አስታውቋል።

ብሔራዊ ባንክ፤ የ“ፋይዳ” ዲጂታል መታወቂያ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ በአስገዳጅነት ጥቅም ላይ እንዲውል ያዘዘው ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ሕዳር 17/2017 ዓ.ም. ለሁሉም ባንኮች በጻፈው ደብዳቤ ነው።

እያንዳንዱ ሰው የሚለይበት ባለ 12-አሃዝ ልዩ መለያ ቁጥር እንዲያገኝ የሚያስችለው የ“ፋይዳ” መታወቂያ፤ የነዋሪዎች የባዮሜትሪክ መረጃዎችን በመውሰድ ምዝገባ የሚደረግበት ስርዓት ነው።

የጣት አሻራ፣ አይን አይሪስ ስካን እና የፊት ምስል ነዋሪዎች መታወቂያውን ለማግኘት የሚያቀርቧቸው የባዮማትሪክ መረጃዎች ናቸው።

እስካሁን ድረስም ከ10 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ይህንን የዲጂታል መታወቂያ ለማግኘት እንደተመዘገቡ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም መረጃ ያመለክታል።

“የፋይዳ” ዲጂታል መታወቂያ “አንድ ሰው አንድ ማንነት” እንዲኖረው የማድረግ ዓላማ ያለው ሲሆን ነዋሪዎች የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት መታወቂያውን መጠቀም ይችላሉ።

በ2015 ዓ.ም. የወጣው የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ አዋጅ፤ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ፈቃድ ያገኙ አካላት አገልግሎት ለመስጠት የዲጂታል መታወቂያን “አስገዳጅ ቅድመ ሁኔታ” ማድረግ እንደሚችሉ ይደነግጋል።

ብሔራዊ ባንክ፤ የ“ፋይዳ” መታወቂያ በአስገዳጅነት ጥቅም ላይ እንዲውል ያደረገው “የፋይናንስ ስርዓቱን ታማኝነት እና ደህንነት” ለማሳደግ እንደሆነ ለባንኮች በጻፈው ደብዳቤ ላይ ተጠቅሷል።

“የፋይናንስ ማጭበርበሮችን መከላከል” እና “የዳታ ባለቤትነት እና ጥበቃን ማረጋገጥም” የባንክ አገልግሎት ለማግኘት የ”ፋይዳ” መታወቂያን ማቅረብ ግዴታ ከሆነባቸው ምክንያቶች መካከል ናቸው።

እነዚህን ምክንያቶች የጠቀሰው ብሔራዊ ባንክ፤ የባንክ አካውንት የሚከፍቱ ደንበኞች የፋይዳ መታወቂያ ማቅረብ ግዴታ እንዲሆን መወሰኑን በደብዳቤ አስታውቋል።

ይህ አስገዳጅ አሰራር በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው በተለያየ ጊዜ እንደሆነም ባንኩ ገልጿል።

የብሔራዊ ባንክ ደብዳቤ እንደሚያስረዳው አዲሱ አሰራር ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው በአዲስ አበባ ከተማ ነው።

ከቀጣዩ ወር ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ደንበኞች የባንክ አካውንት መክፈት የሚችሉት የ“ፋይዳ” ዲጂታል መታወቂያ ሲያቀርቡ እንደሆነ የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አማካሪ የሆኑት ማርታ ኃይለማርያም ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ከአምስት ወራት በኋላ በሰኔ 24/2017 ዓ.ም. ደግሞ ይህ አስገዳጅ አሰራር በሀገሪቱ “ዋና ዋና ከተሞች” ተግባራዊ መሆን እንደሚጀምር በብሔራዊ ባንክ ደብዳቤ ላይ ሰፍሯል።

በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ደንበኞች የባንክ አካውንት ለመክፈት የ”ፋይዳ’ ዲጂታል መታወቂያን በአስገዳጅነት መጠየቅ የሚጀምሩት ደግሞ ከአንድ ዓመት በኋላ ከታህሳስ 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ነው።
ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ከባንክ አግልግሎት ጋር በተያያዘ ”ፋይዳ” የሚጠየቀው አካውንት ለመክፈት ቢሆንም በአጠቃላይ የባንክ አገልግሎት ለማግኘት ዲጂታል መታወቂያ መያዝ ግዴታ መሆን የሚጀምርበት ጊዜንም ብሔራዊ ባንክ አሳውቋል።

ከሁለት ዓመት በኋላ ከታህሳስ 2019 ዓ.ም. ጀምሮ አዲስ አካውንት ከሚከፍቱ ውጪም ያሉ ነባር ደንበኞች ጭምር ደንበኞችም ዲጂታል መታወቂያ ሊኖራቸው እንደሚገባ ለባንኮች ተገልጿል።

ባንኮች፤ ይህንን የጊዜ ሰሌዳ እና አስገዳጅ አሰራሮችን “በጥብቅ እንዲከተሉ” ብሔራዊ ባንክ አሳስቧል።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው የዳሽን ፕሬዝዳንት አቶ አስፋው አለሙ እና ሲንቄ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ነዋይ መገርሳ ብሔራዊ ባንክ አገልግሎት ለማግኘት የ”ፋይዳ” መታወቂያ አስገዳጅነት እንዲጠየቅ መወሰኑን በበጎ እንዲመለከቱት ተናግረዋል።

“አንድ ሰው አንድ ማንነት” እንዲኖረው የሚያደርገው ይህ አሰራር ባንኮች የሚያጋጥማቸውን የማጭበርበር ወንጀል ለመግታት ይረዳል የሚል ተስፋቸውን ገልጸዋል።

ይሁንና ፕሬዝዳንቶቹ የዲጂታል መታወቂያው ህዝብ ጋር የመድረሱ ጉዳይ ተግዳሮት ሊሆን እንደሚችል ሳይጠቅሱ አላለፉም።

“ህዝቡ [መታወቂያውን] በደንብ ወስዶታል ወይ የሚለውን ስናይ ይህ ትንሽ ተግዳሮት ሊሆን ይችላል” የሚሉት የሲንቄ ባንክ ፕሬዝዳንቶ አቶ ነዋይ፤ ለዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ የሚውሉት መሳሪያዎች “በብዛት አለመኖርም” ሌላኛው ስጋት መሆኑን አንስተዋል።

የጣት አሻራ ለመውሰድ እና የአይን አይሪስ ስካን ለማድረግ የሚውሉት እነዚህ መሳሪያዎች ለመግዛት ባንኮች ገንዘብ በማዋጣት በማህበራቸው በኩል እንዲገዛ ለማድረግ ሂደት መጀመራቸውን የሚያስታውሱት አቶ ነዋይ፤ እስካሁን ድረስ “ግዢው እንዳልተጠናቀቀ” አስረድተዋል።

“[አስገዳጁን አሰራር ለመተግበር] ቀነ ገደብ ተቀምጦ መሳሪያዎቹ ከሌሉ ተግዳሮት እንዳይፈጠር የሚያሰጋው እርሱ ነው። ከዚያ ውጪ ግን ብሔራዊው መታወቂያ ጠበቅ ብሎ መምጣቱ ለባንኮች በጣም ነው የሚጠቅመው” ብለዋል።

የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አማካሪ የሆኑት ማርታ ግን በቀጣዩ ወር በአዲስ አበባ ከተማ የአስገዳጁ አሰራር ትግበራ ላይ “ብዙ ችግሮች ያጋጥማል” የሚል ስጋት እንደሌለ ተናግረዋል።

አማካሪዋ ለዚህም በምክንያትነት የጠቀሱት አንዱ ጉዳይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽህፈት ቤት “በዘመቻ” ነዋሪዎች መታወቂያውን እንዲያወጡ እያደረጉ መሆኑን ነው።

ለ”ፋይዳ” ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባው የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች ጉዳይም “በቅርብ ጊዜ” እንደሚፈታ ገልጸዋል።

“ባንኮች በማህበር በኩል ወደ ስድስት ሺህ መሳሪያዎች በቅርቡ ይገዛሉ። እነዚያ [መሳሪያዎች] የሚከፋፈሉት ባንኮች ባላቸው ቅርንጫፍ መጠን ስለሆነ ሁሉም ጋር ይዳረሳል። ዲጂታል መታወቂያ የሌለው ሰው ሲመጣ እዚያው መዝግበው አካውንት መክፈት ይችላሉ” ሲሉ አስረድተዋል።
ሰላም ለሀገራችን @EwunetMediaOfficial

2 - 0