የሚስጥረ ማህደር ካሁን በፊት ካሳተምኩት የሕይወት ጉዞ (the journey of life) ከሚለው መጽሐፍ የቀጠለ ነው። መነሻ ዓላማው ወላጆቻቸውን በሕፃንነት ዕድሜ አጥተው ለጉዲፈቻ ተሰጥተው ከአገራቸው ውጭ ያሉትን ኢትዩጵያዊያንን የሚገልጽ ነው። ራሄል፣ አይዳ፣ ሱዛንና መኮንን የዚህ ክፍል አካል ናቸው። ያለፉበት የሕይወት መንገድ አስቸጋሪ ሆኖ ቢያገኙትም ተስፋ ሳይቆርጡ አሳዳጊዎቻቸውን አክብረውና አስመስግነው ስኬታማ ለመሆን የበቁ ናቸው። የሕይወት ልምዳቸውና ታታሪነታቸው በዚህ ዘመን ላሉ ወጣቶች አበረታች ሆኖ የቀረበ ነው። ጽሑፉን ለማስተዋወቅ በትረካ መልክ በከፊል የቀረበ ሲሆን ጊዜው ሲፈቅድ ታትሞ ለገበያ ይቀርባል።
ደራሲው ተክለማርያም ቢርቢርሳ።
Mistre's archive is a continuation of my previously published book, The Journey of Life. Its original purpose is to describe Ethiopians who lost their parents in infancy and were given up for adoption abroad. Rachel, Aida, Suzanne and Mekonnen are part of this class. Even if they find the life path they have passed through difficult, they are able to respect and thank their guardians without giving up and succeed. Their life experiences and hard work are an inspiration to the youth of today.
Author Teklemariam Birbirsa.